አዋሽ ባንክ ከዴሎይት ጋር በመተባበር “የሳይበር ደህንነት የሁሉም ህልውና ሃላፊነት ነው” መሪ ቃል የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር አካሄደ
#FastMereja I አዋሽ ባንክ ከዴሎይት ኢንቨስትመንት ጋር በመተባበር “የሳይበር ደህንነት የሁሉም ህልውና ሃላፊነት ነው” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ የባንኩ መዋቅሮች ውስጥ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር ማካሄድ መጀመሩን አስታወቀ። ይህንን አጠቃላይ የባንኩን የሳይበር ደህንነት ማስተዋወቂያ መርሃ-ግብር በተመለከተ የተዘጋጀው የምክክር መድረክ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም በኢሊሊ ሆቴል ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሀይ ሰለሞን እንደገለጹት፤ የሳይበር ደህንነት አገልግሎቶችን የበለጠ ተደራሽ፣ ጥንቁቅ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የባንኩን አሰራር ማሻሻል ቀጣይነት ያለው ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው። የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አክለውም የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል የተቀናጀ የጸረ-አደጋ ዝግጅት ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብሩ የአዋሽ ባንክን አገልግሎቶች በመጠበቅ፣ ደንበኞች እያደረጉት ያለውን የዲጂታል ጉዞ በዘላቂነት ለመደገፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ መርሃ-ግብር ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የባንኩ ስራ አመራር አባላት፣ ሰራተኞች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በሂደቱም አሁን ላይ እየታዩ ያሉ የሳይበር ስጋቶችን ለመቀነስ፣ በተግባር ሊተገበሩ የሚችሉ ጠንካራ የደህንነት ባህሎችን በባንኩ ውስጥ ለማስረጽ ከፍተኛ ጥረት እንደሚደረግ ተገልጿል። ባንኩ ከዴሎይት ጋር በመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሳይበር ደህንነት ልምዶችን በማስተዋወቅ ረገድ የተሻለ አቅም ለመፍጠር እየሰራ መሆኑ በጉባኤው ተመላክቷል።
በመጨረሻም የሳይበር ደህንነት የሁሉም የባንኩ ባለድርሻ አካላት የጋራ ሃላፊነት መሆኑ ተረጋግጦ፤ ንብረቶችን ለመጠበቅ፣ የደንበኞችን ምስጢራዊነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የተሟላ እና አስተማማኝ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት በሚደረገው ጥረት ላይ ቁርጠኛ አቋም እንዳለ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል።




