banner

የማሽነሪ ኢንቨስትመንት ወርክሾፕና የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

#FastMereja I የማሽነሪ ገዢዎችን፣ አቅራቢዎችን፣ ኢንቨስተሮችንና የፋይናንስ ተቋማትን በአንድ መድረክ ለማገናኘት ያለመ የማሽነሪ ኢንቨስትመንት ወርክሾፕና የሞባይል መተግበሪያ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ። ከመግዛትዎ በፊት ይማሩ፣ ኢንቨስት ከማድረግዎ በፊት ያቅዱ በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው ይህ መርሃ ግብር፣ በስራ ሰው ፕሮፐርቲ ኤንድ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አዘጋጅነት የቀረበ ነው።

በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው፣ በዘመናዊው የንግድ ዓለም ስኬት በገንዘብ አቅም ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በትክክለኛው መረጃ፣ በጥንቃቄ በተደረገ የኢንቨስትመንት ውሳኔ እና በጠንካራ የንግድ ትስስር ላይ የተመሰረተ ነው። በተለይም ማሽነሪ ለመግዛት ሲታሰብ የማሽኑ ጥራት፣ አቅም፣ የሥራ ብቃት፣ የጥገና ወጪ፣ የመለዋወጫ እቃዎች አቅርቦት፣ የተሰለጠነ የሰው ኃይል እና የፋይናንስ አማራጮች በጥንቃቄ መገምገም የሚጠይቁ ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸው ተነስቷል።

ድርጅቱ ገዢዎችን፣ ሻጮችን፣ ኢንቨስተሮችንና የንግድ ባለቤቶችን በማገናኘት በዘርፉ ያለውን የመረጃና የትስስር ክፍተት ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

በወርክሾፑ ላይ የሂታቺ፣ ኤክስ ኤም ጂ፣ ሳኒ እና ሻንቲ ጂቤል ጃብ ኢንጂነሪንግ የቴክኒክ ባለሙያዎች የማሽነሪ ምርቶችንና የቴክኒክ አቅሞቻቸውን የሚመለከቱ ገለጻዎችን አቅርበዋል።





Leave a Comment