#FastMereja I በኢትዮጵያ በዘመናዊ የጥርስ ሕክምና ዘርፍ ለተከታታይ 10 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ዳሊያን የጥርስ ሕክምና ልዩ ክሊኒክ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያላቸውን ወጣቶች ልጅ ዳውድ እና ባሪዮና ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መረጠ። ክሊኒኩ ባለፉት ሦስት ወራት ከገበያ ጥናትና ማህበራዊ ሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ያደረገውን ዝግጅት አጠናቆ የብራንድ አምባሳደሮቹን ይፋ አድርጓል።
ዳሊያን የጥርስ ሕክምና ልዩ ክሊኒክ እንዳስታወቀው፣ የሁለቱ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መመረጥ በማህበራዊ ሚዲያ ባላቸው ከፍተኛ ተቀባይነት፣ ተወዳጅነትና ከተከታዮቻቸው ጋር ባላቸው አዎንታዊ ግንኙነት ላይ የተመሠረተ ነው። አዲሱ የትብብር ስምምነት ከተለመደው የማስታወቂያ ሥራ ባለፈ የማህበረሰቡን የአፍና ጥርስ ጤና ግንዛቤ ለማሳደግ፣ የሕክምና ተደራሽነትን ለማስፋትና የደንበኞችን እምነት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
አምባሳደሮቹ ልጅ ዳውድ እና ባሪዮና በተሰጣቸው ኃላፊነት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ ከወላጆች፣ ከትምህርት ቤቶችና ከጤና ተቋማት ጋር በመተባበር ስለ አፍና ጥርስ ጤና አጠባበቅ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ላይ በተገቢው መንገድ እንደሚንቀሳቀሱ አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ለማካሄድ መታቀዱን የክሊኒኩ መረጃ ያመለክታል።
ዳሊያን የጥርስ ህክምና ልዩ ክሊኒክ በወጣቷ ኤክስፐርት ዴንታል ሰርጅን ዶ/ር ፈርሃን አደም የሚመራ በ2008 ዓ.ም የተመሰረተ ላለፉት 10 ዓመታት አገልግሎቶች እየሰጠ ያለ ተቋም ነው።
ቀደም ሲል ሶማሌ ተራ አካባቢ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ ብዙዎችን በህክምና አገልግሎቱ ተደራሽ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ለትራንስፖርት እጅግ አመቺ በሆነው የመዲናችን አካባቢ መሃል ቦሌ መድሃኔዓለም አጠገብ ኖህ ሪልስቴት ህንጻ 6ኛ ፎቅ የተንጣለለ ወለል ላይ የሚገኝ ዘመናዊ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ነው::





2 comments
ere ambassador mndnw koye lela neger hone ende
እኔ የታየኝ በረከት ነው እጅግ ፈጣን ተግባቢ ጎበዝ ልጅ