0
#FastMereja I የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አምራቾችን እንዲሁም የዘርፉን ተዋናዮች ያሰባሰበው የአፍሪካ ምንጮች፣ የፋሽን ሳምንትና የቆዳ ትርኢት (2026) በዛሬው ዕለት በይፋ ተከፈተ። ትርኢቱ የኢትዮጵያን የጨርቃጨርቅ፣ አልባሳት፣ ጫማ እና የቆዳ ኢንዱስትሪዎች አቅም ለማስተዋወቅ እንዲሁም የሀገር ውስጥ አምራቾችን ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ነው።
በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ፣ ኢትዮጵያ ለንግድና ለኢንቨስትመንት ክፍት መሆኗን በመግለጽ ዓለም አቀፍ ብራንዶችና ባለሀብቶች በዘርፉ ያለውን ምቹ ሁኔታ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል። ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት ባለፈ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን በማምረት የእሴት ሰንሰለቱን የማጠናከር ግብ መያዙን የጠቀሱት ሚኒስቴር ዴኤታው፣ የሞጆ ሌዘር ከተማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፕሮጀክት ለዚህ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አስረድተዋል።
የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች እንዲሁም የልማት አጋሮች የተሳተፉበት ይህ መድረክ፣ ዘላቂ የገበያ ትስስር፣ የእውቀት ሽግግርና የንግድ አጋርነት ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።





1 comment
Veronica Adane (Hollywood reward gifts for fans
Thank you My fans (two music released.) ልማልልህ I Swear my promise and Only you ኔፔ ሃራ Wolatia Music.