0
#FastMereja I የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን የዓለም አቀፉ የሥርዓተ-ምግብ ማሻሻያ ንቅናቄ የመሪዎች ቡድን አባል አድርገው ሾመዋል። ይህ ሹመት በዓለም አቀፉ የምግብ ዋስትና እና የሥርዓተ-ምግብ አስተዳደር ዘርፍ ታዋቂ የአፍሪካ ድምፅ እንዲወከል የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ዋና ጸሐፊው እ.ኤ.አ ህዳር 17 ቀን 2026 በጻፉት ይፋዊ ደብዳቤ፣ መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የያዳም ፋውንዴሽን መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ደመቀ፣ የምግብ ዋስትናንና ሥርዓተ-ምግብን ለማሻሻል ላሳዩት ጠንካራ ቁርጠኝነት እውቅና በመስጠት ይህን ከፍተኛ ኃላፊነት እንዲቀላቀሉ ጋብዘዋቸዋል።
ሹመቱ እ.ኤ.አ ከህዳር 1 ቀን 2026 ጀምሮ ተፈጻሚ ሆኖ እስከ ታህሳስ 31 ቀን 2028 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

2 comments
ይገባዋል ቅን ሰው
አሰይ ከምክትልነት ይሻለዋል