banner

የ2017 እንቁጣጣሽ “ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017” ሊካሄድ ነው።

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን በ62 ሚሊዮን ብር ጨረታውን በማሸነፍ የ2017 እንቁጣጣሽ አዲስ አመት ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

የኤክስፖ ታይትል ስፖንሰርሺፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ስያሜውም “ሲቢኤ ብር ኤክስፖ 2017″ በሚል ስያሜ መሆኑ ተገልጿል።

ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለ21 ተከታታይ ቀናት የሚከናወነው “ሲቢኢ ብር ኤክስፖ” የፋይናንስ መንደር፣ የመዝናኛ መንደር፣ የቴክኖሎጂ መንደር፣ የባህል መንደር፣ የገበታ መንደር፣ የዕውቀት መንደር ወዘተ በማለት በተከፋፈሉ መንደሮች ሸማቾችና ጎብኚዎች የፈለጓቸውን ምርቶችንና አገልግሎቶችን በመገኛ አድራሻቸው በመሔድ መጎብኘትና መሸመት ይችላሉ ተብሏል።

ከአራት መቶ በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ድርጀቶች የሚሳተፍበት “ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017″ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይጎበኘዋል ተበሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለጎብኚዎች ወደ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሲቢኢ ብር በኩል በቆረጡት የ100 ብር ትኬት አማካኝነት የሚያገኙትን የዕጣ ቁጥር በመጠቀም እንደ እድላቸው የ5 ሺህ ፣ የ10ሺ፣ የ50ሺ፣ የ100 ሺ ብር ዋጋ ያላቸውን ኩፖኖችን በማሸነፍ ከኢግዚቢሽኑ የፈለጉትን ዕቃ መሸመት የሚችሉበት የዕጣ ጨዋታ ተዘጋጅቷል።

ከኩፖኖቹ በተጨማሪ አንድ የኤሌክትሪክ ባይክ እና 2.3 ሚሊዮን ብር ዋጋ የሚያወጣ አዲስ የቤት አውቶሞቢል መኪና ለባለዕድለኞች በሽልማትነት መቅረቡን ተገልጿል።

በኤክስፖ መክፈቻ እና መዝጊያ ላይ ከሚኖረው የሙዚቃ ዝግጅት በተጨማሪ ቅዳሜ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ድምጻዊ አብርሃም ገብረ መድህን ጨምሮ እውቅ ድምጻዊያን በታዋቂ ባንድ በመታጀብ የሚያቀነቅነበትን ልዩ ኮንሰርትን ተዘጋጅቷል።

“ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017″ ታሜሶል ኮሙኒኬሽን እና ሊያን ቢዝነስ ግሩፕ ከአሴንቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር አዘጋጅቶታል።

Leave a Comment