ቢዩ ዴሊቨሪ በወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ሕፃናት ማቆያና ተሃድሶ ተቋም በመገኘት የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አከናወነ።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው በወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ሕፃናት ማቆያና ተሃድሶ ተቋም ከ9 አመት እስከ 15 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ በማወቅ አልያም ባለማወቅ በተለያዩ ወንጀል ውስጥ ገብተው የተገኙ ታዳጊዎች ማቆያ እንደሆነ የተቋሙ የግቢ ተቆጣጣሪ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጪምዴሳ ነገሳ ለፋስት መረጃ ገልጿል።

ቢዩ ዴሊቨሪ የተመሰረተበትን ሶስተኛ አመት ምክንያት በማድረግ የቢዩ ዴሊቨሪ ጋር አብሮ ከሚሰሩ ሬስቶራንቶች ጋር አብሮ በመሆን የሕፃናት ተሃድሶ ተቋም በመገኘት የማዕድ ማጋራት አከናውኗል።

አቶ ብሩክ ገነነ የቢዩ ዴሊቨሪ የማርኬት እና የቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ኃላፊ ነው ዛሬ ያጋራነው የማዕድ ማጋራት በጣም የሚያስደስት ነው ከገንዘብም አልፎ የምናገኘውን ነገር እንዴት አድርገን ወደ ህብረተሰቡ እናስተላልፍ የሚለው ነገር ላይ ነው ማተኮር የፈለግነው ዛሬ ያየነው ደስታ በየጊዜው አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን ግንዛቤ ሰጥቶናል ብሏል።

በተቋሙ ውስጥ ታዳጊዎቹ ከፀባይ ማረሚያ በተጨማሪ መደበኛ ትምህርት እስከ 8 ክፍል የሚማሩ ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ የሞያ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አቶ ጪምዴሳ ገልጸውልናል።
በአሁኑ ወቅት 13 ሴቶች እና 61 ወንዶች በተቋሙ ይገኛሉ።

የማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙን የደገፉ ሬስቶራንቶች ፋ ፍሬሽ ሬስቶራንት፣ ኩኩሉ ቺክን፣ ሲፕል ፒስትሮ፣ ቦስ በርገር፣ ቬጋስ በርገር፣ ድሪምስ ቺክን እና ዲቫይን በርገር ሲሆን ለደገፉት ሬስቶራንቶች ቢዩ ዴሊቨሪ ምስጋና አቅርበዋል።
ቢዩ ዴሊቨሪ ከ900 ሬስቶራንቶች ጋር የሚሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ500 በላይ በሳይክል የዴሊቨሪ ስራ የሚሰሩ አባላት ሲኖሩት በአጠቃላይ ለ600 ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ተቋም ነው።