banner

ሲቢኤ ብር+ የ2017 እንቁጣጣሽ ኤክስፖ ተከፈተ

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር+ እንቁጣጣሽ አዲስ አመት ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ዛሬ ነሃሴ 16/2017 ዓ.ም ጥሪ በተደረገላቸው የክብር እንግዶች በኤግዚብሽን ማዕከል ተከፈተ።

ከነሐሴ 16 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከናወነው “ሲቢኢ ብር ኤክስፖ” የፋይናንስ መንደር፣ የመዝናኛ መንደር፣ የቴክኖሎጂ መንደር፣ የባህል መንደር፣ የገበታ መንደር፣ የዕውቀት መንደር ወዘተ በማለት በተከፋፈሉ መንደሮች ሸማቾችና ጎብኚዎች የፈለጓቸውን ምርቶችንና አገልግሎቶችን በመገኛ አድራሻቸው በመሔድ መጎብኘትና መሸመት ይችላሉ ተብሏል።

ከአራት መቶ በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ድርጀቶች ተሳታፊ የሚሆኑበት “ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017″ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይጎበኘዋል ተበሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለጎብኚዎች ወደ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሲቢኢ ብር በኩል በቆረጡት የ100 ብር ትኬት አንድ የኤሌክትሪክ ባይክ እና BWD አዲስ የቤት አውቶሞቢል መኪና ለባለዕድለኞች በሽልማትነት መቅረቡን ተገልጿል።

በኤክስፖ በዝነኛ የሙዚቃ ባንዶች ታዋቂ ድምፃዊያን የሙዚቃ ስራቸውን አጋፔ ኤቨንት አሰናድቶ የሚያቀርቡ ይሆናል።

Leave a Comment