banner

71ሺ ዶላር የመለሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ

አቶ ለማ በቀለ አለሙ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴኪዩሪቲ ክፍል ውስጥ የሚሰሩ የሥራ ባልደረባ ሲሆኑ በሥራ ገበታቸው ላይ በነበሩበት ወቅት አንድ መንገደኛ ረስተዉ የሄዱትን የእጅ ቦርሳ ውስጡ ከነበረው 71 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ጋር ምንም ሳያጎድሉ በሙሉ ለሚመለከተው የአየር መንገድ ቢሮ ያስረከቡ ሲሆን፤ አየር መንገዱም አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ንብረቱ ለባለቤቱ እንዲመለስ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጀመንት አባላት እና ሠራተኞች ለዚህ መልካምና አርዓያነት ላለው ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment