banner

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ስራ ማህበር በመቀለ ከተማ የመጀመሪያ ቅርንጫፍ ቢሮውን ከፈተ!!!

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበር የመጀመሪያ ቅርንጫፍ ቢሮውን በትግራይ ክልላዊ መንግስት መቐለ ከተማ ኖታ ህንፃ ላይ በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ አስመርቆ ከፍቷል። በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይም ፕሮፌሰር ክንደያ ገ / ህይወት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ሽግግር ሴክሬያት ኃላፊ፣ አቶ ነጋ አሰፋ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኅብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ኃላፊ፣ የህብረት ስራ ማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም አብርሃ፤ የኅብረት ስራ ማኅበሩ የቦርድ አባላት ፤ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የኅብረት ስራ ማኅበሩ አባላት እና ሰራተኞች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል። በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ አቶ ነጋ አሰፋ እንደገለፁት አሚጎስ ወደ ትግራይ ክልል በመምጣቱ የተዳከመውን ኢኮኖሚ እንደሚያነቃቃ በመግለፅ ክልሉ ላይ ያሉ ህብረት ስራ ማህበራትም ከአሚጎስ ጋር በጋራ በመሆን የተሻለ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።





2 comments

Emnet Tesfa Fikir August 24, 2024 - 1:24 pm

የኢትዮጵያን መለያ ቀለማት መጠቀም የማይፈልጉት ነገር ግራ የሚገባ ነው

Reply
Eli Jah August 24, 2024 - 1:27 pm

የሻሼን ቀብርስ ዘግቡንጂ😀

Reply

Leave a Comment