banner

70 ዓመት እስራት

በባድ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በ70 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ።
#FastMereja
ሳሙኤል ሀይሉ እና ሳቢር ከድር የተባሉት ተከሳሾች በተለያዩ ጊዜያት የስርቆት ወንጀሉን የፈፀሙት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ነው።

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ማስተባበሪያ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር በልሁ ወልደኢየሱስ እንደገለፁት ተከሳሾቹ የግለሰቦችን መኖሪያ ቤት እና የንግድ ቤቶችን በር በመገንጠልና በተመሳሳይ ቁልፍ ከፍተው በመግባት ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ቴሌቪዥኖች እና ሌሎች የተለያዩ እቃዎችን ሰርቀው ወስደዋል።

ፖሊስ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ባከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የተሰረቁትን ንብረቶች ማስመለሱን የጠቀሱት የምርመራ ሃላፊው፤ እነዚህን ንብረቶች ከወንጀል ፈፃሚዎቹ እየተቀበለች በቤቷ ውስጥ ደብቃ ስታስቀምጥ የነበረች ትዕግስት ስመኝ የተባለች ግለሰብ ተይዛ ምርመራ እንደተጣራባትም አስረድተዋል።

በሶስቱ ተከሳሾች ላይ በአጠቃላይ ዘጠኝ የክስ መዝገብ የተደራጀባቸው ሲሆን ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በአምስቱ መዝገቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም መሠረት ተከሳሽ ሳሙኤል ሀይሉ በእያንዳንዱ 5 የክስ መዝገቦች ላይ የተሰጠው ውሳኔ በድምሩ ሲሆን ፣ በሁለተኛ ተከሳሽ ሳቢር ከድር ላይ በእያንዳንዱ 5 የክስ መዝገቦች በድምሩ የ65 ዓመት እስራት ቅጣት መወሰኑን ዋና ኢንስፔክተር በልሁ አስረድተዋል።

የተሰረቁትን ንብረቶች በመሸሸግ ወንጀል የተከሰሰችው ትዕግስት ስመኝ ከአምስቱ የክስ መዝገቦች በአራቱ በእያንዳንዱ የሶስት አመት እስራት እንድትቀጣ እና ቅጣቱ በገደብ እንዲሆንላት የተደረገ ሲሆን በአንደኛው መዝገብ በተመሳሳይ በ 3 አመት እስራት እንድትቀጣና ቅጣቷን ማረሚያ ቤት ሆና እንድትፈፅም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉን የምርመራ ሃላፊው አብራርተዋል።

ተከሳሾቹ ከተደራጀባቸው ዘጠኝ የክስ መዝገቦች መካከል ውሳኔ ያላገኙት ቀሪ 4 መዝገቦች በሂደት ላይ እንደሚገኙም ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ነው የዘገበው።





10 comments

Eyu Lala August 24, 2024 - 11:10 am

😁 ሞተውም ሬሳው እስራቱን ካልጨረሰ አይወጣም😂😂😂ሀገረ ኢትዮጵያ

Reply
Sami Z Habesha August 24, 2024 - 11:11 am

የእድሜ ልክ አይሏቸውም🤔
ሞተውም አስክሬናቸው አይወጣም ማለት ነው😁

Reply
Dere Dawit August 24, 2024 - 11:11 am

የወንጀል መቅጫ ህግ ተሻሽሎ ነው ?

Reply
KB Diplomatic Leader August 24, 2024 - 11:11 am

ኣየ ኢትዮጵያ 😥ህፃን ልጅ ደፍሮ በኣሰቃቂ ሁኔታ በ 25 ኣመት እየተቀጣ ፣ንብረት የዘረፈ ደግሞ በ 70 ኣመት 😥ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የህግ አካላት ስብሰቦ ነበር ማቃ*ል። ከሰው ህይወት በላይ ዘንባባ የሚከበርባት።

Reply
ቼልሲ ያያ August 24, 2024 - 11:11 am

👍

Reply
ኦኣሲስ O'𝕒𝕤𝕚𝕤 August 24, 2024 - 11:11 am

70 ዓመታት 😂😂😂😂 ጀዝባ ዳኛ

Reply
Abel Yigezu August 24, 2024 - 11:12 am

እር ተው 70 ዓመት እስራት ሚባለ ነገር የለም በኢትዮጵያ ህግ

Reply
Bezawork Hailu August 24, 2024 - 11:12 am

ኧረ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ 70 ዓመት ብሎ የለም😁…. በቁጥር ደረጃ ጣሪያው 25 ዓመት ነው ። ከዛ በላይ ከሆነ ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ነው።

Reply
Ta Ta Lali August 24, 2024 - 11:13 am

በየትኛው ወንጀል መቅጫ ነው መቼስ ኢትዮጵያ የላትም

Reply
Henok Mulugata August 24, 2024 - 11:13 am

ይሄ ዳኛ ይፍረድ ስለ ሄቨን

Reply

Leave a Comment