0
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደገም ወረዳ አስተዳደር ከጥቂት ወራት በፊት በሚሊሺያነት ሰልጥነው ካለ ትጥቅ የተበተኑ ሰዎች የታጣቂዎች ኢላማ እንደሆኑ መሠረት ሚድያ ዘግቧል።
እነዚህ በቁጥር 230 የሚሆኑ ሚሊሺያዎች ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ ያለምንም ትጥቅ እና ስምሪት ወደየ ቤታቸው ተበትነው ነበር ተብሏል።
“ከዛ ግን ይህ ስልጠና መሰጠቱን የሚያውቁት ጫካ የሚገኙት ታጣቂዎች ከተመረቁበት ማግስት ጀምሮ ከመሃል ከተማ እየለቀሟቸው ሲወሰዷቸው ነበር፣ አንድም ሃይ የሚል የፀጥታ አካል አልነበረም” ያሉ ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች ለመሰረት ሚዲያ ተናግረዋል።
“ሁሉም እያየ እንዳላየ እየሆነ ነበር፣ ቢያንስ ከሰለጠኑት 230 ገደማ ሰዎች ያልተወሰዱት 17 ሚሊሻዎች ብቻ ናቸው” ያሉት ምንጮቹ ታጋች ሚሊሺያዎች ከ150 ሺህ ብር እስከ 500 ሺህ ብር እየከፈሉ እንደተለቀቀ ተናግረዋል።
“ከሁለት ያጡ ሆነው እየተሰቃዩ ነው፣ የአካባቢው ሰው ይህን በደንብ ያውቃል” ብለዋል።
ዘገባው የመሰረት ሚዲያ ነው።

5 comments
ልሳቅ ቀልድ ነዉ እንዴ😂😂😂
ይሄማ አያስቅም😑
አሪፍ ዋጋ ነው🤒
አይ አቢይ
እኮ መንግስት ያሰለጠናቸው በታጣቂዎች ታገቱ ነው የሚትለን😲😲
➡ሚሽቱን የሳቅ ያድርግልን…🙏🙏🙏