0
“የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት እንደማልደግፍ ተደርጎ በመነገር ላይ ያለው ሀሳብ ሀሰት ነው፣ ስም ማጥፋት ነው” ሲሉ ህወሓትን በመወከል በፕሪቶርያ ተደራዳሪ የነበሩት እና በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው የህወሓት ቡድን ውስጥ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ፍስሃ ሃፍተፅዮን (ዶ/ር) ገልጸዋል።
የፕሪቶርያው ስምምነት በተፈረመበት ወቅት “ትግራይን ወክለው በተሳተፉ ተወካዮች መካከል ከፍተኛ ልዩነት” እንደነበረ ያወሱት ስራ አስፈጻሚው “በወቅቱ ሁሉም ተስማምቶ ስምምነቱ መፈረሙ አንድ ጸጋ ሲሆን ቀሪ ጉድለቶችን ደግሞ በሂደት እንሞላቸዋለን የሚል እምነት ነበረን” ብለዋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አንድ አመት ከአምት ወራት ቢያስቆጥርም “በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋምን በተመለከተ በፕሪቶርያው ስምምነት የመጀመሪያ ሰነዶች ውስጥ አልነበረም፣ በኋላ ላይ በሂደት ነው የተካተተው፣ በወቅቱ ለምን ብለን ሞግተናል” ሲሉ ገልጸዋል፤ “የጊዜያዊ አስተዳደሩ እድሜም ከስድስት ወር እስከ አንድ አመት ጊዜ ብቻ” መሆኑን አውስተዋል።
Via አዲስ ስታንዳርድ

10 comments
እምሳም በለው
sim neberachihu malet new? min aynet sim?
ለሰልጣን ጥማችሁ ሕዝቡን ያሰከፈላችሁ የህወይት ወጋ ይበቃችኋል አሁን ለህዝቡ ማሰብ ያሰጋል ተረጋጉ ።
ደጺ እኮ ኤርትራዊ ነች ከጌች ጋር ወደፊት✊
Bexam nw yasasebachewu 😂😂😂
Tabadu balachaw
ሰላም ከሁሉም ይበልጣል ሰይጣን::
ጀዝባ ስብስብ
ከአንድ ስልጣን ፈላግ የምጠብቅ ቁልጭ ያለች ንግግር😂😂😂
በፕርቶሪያ ስምምነት መሰረት ህወሀት ፈርሷል