banner

ማኑዌል ኡጋርቴ ከሊቨርፑሉ አስፈሪ ሽንፈት በሗላ ማን.ዩናይትድን ወደ ትክክለኛው መንገድ ለማምጣት በውድድር ዘመኑ ቡድኑን መስ

ማኑዌል ኡጋርቴ ከሊቨርፑሉ አስፈሪ ሽንፈት በሗላ ማን.ዩናይትድን ወደ ትክክለኛው መንገድ ለማምጣት በውድድር ዘመኑ ቡድኑን መስመር ለማስያዝ “ይፋለማል”::

በእሁዱ ጨዋታ በሊቨርፑል ብልጫ የተወሰደበት የማን.ዩናይትድ መሀል ክፍል የኡሩጓዩን እውቅ መንፈስ “Garra Charrúa” (ጋራ ቻሩዋ) ወደ ማን.ዩናይትድ እንደሚያመጣ ተስፋ ሰንቋል ቃልም ገብቷል ማኑዌል ኡጋርቴ::

በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ እየተቸገረ ላለው ዩናይትድ የአሸናፊነት መንፈስ በማምጣት ሂደት የኤሪክ ቴን ሃህ ቡድን ከኡጋርቴ ብዙ ይጠብቃል::

በ 42ሚ.ፓ ከፒኤስዤ ዩናይትድን የተቀላቀለው አዲሱ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች እሁድ ዩናይትድ ሊቨርፑልን ከማስተናገዱ በፊት በኦልድ ትራፎርድ ከደጋፊ ጋር ተዋውቋል በዕለቱ አዲሱ ክለቡ በመራራ የእግር ኳስ ተቀናቃኙ ሊቨርፑል 3 ለ 0 ሲረታ ለማየት ተገዷል::

የቴን ሃህ ቡድን በጨዋታው በፖዜሽን ተበልጧል ደግሞም በብዙ የተጋለጠ ነበር:: ነገር ግን ኡጋርቴ ቃል ገብቷል የኡሩጓውያንን “Garra Charrúa” (ጋራ ቻሩዋ) መንፈስ ተጠቅሞ በአቅሙ ማን.ዩናይትድን በድጋሚ ጠንካራ እንደሚያደርገው::

“Garra Charrúa (ጋራ ቻሩዋ) ማለት ሁሉንም ኳሶች ማሸነፍ እያንዳንዱን ልክ እንደመጨረሻህ ማየት” ይህንን መዋደቅ/ትግል በኡሩጓውያን ተጫዋቾች ታገኘዋለህ ይህ ተፈጥሮ ነው የመጣንበት ነው መነሻችን ነው::” ይላል ኡጋርቴ ይህንን እውቅ አባባል ሲያብራራ::

“ኡሩጓይ ሚጢጢ ሀገር ናት ግን ብዙ ስኬቶች ያሏት:: ጥሩ ተጫዋቾችን ታፈራለች የ “Garra Charrúa” (ጋራ ቻሩዋ) መንፈስ የተላበስን በየትኛውም ሁኔታ ሁሉንም ነገር መስጠት:: ሌላ ትርጉም የለውም መሰረታዊ ሃሳቡ ይህ ነው::”

የኡጋርቴ ትልቁ ጥንካሬው ball recovery ነው (ኳስን መልሶ ማግኘት/የማጥቃት የመጀመሪያው ደረጃ) :: ከ 2022/23 የውድድር ዘመን መጀመሪያው አንስቶ በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች በ 90 ደቂቃ በአማካይ ሁለተኛ ብዙ ኳስ ያስጣለው (ብዙ ሸርተቴዎች ያሉት) ተጫዋች ነው:: በአንድ ወቅት ኡሩጓዊዉ አማካይ እግር ኳስን ሲገልጽ እንዲህ ነበር ያለው “እግር ኳስ ማለት ኳሱን ስትይዘው ጨዋታ ኳሱን ባጣኸው ጊዜ ውጊያ ነው” እናም ዩናይትድን ይህንን ባህሪይ ማላበስ ይፈልጋል::

“ይህንን ስል ከልቤ ነው ምክንያቱም የእኔን የአጨዋወት ዘይቤም እየገለፅኩ ነው ደግሞም ይህንን ማሰብ ተፈጥሯዊ ነው::” የ 23 ዓመቱ ኡጋርቴ ይቀጥላል:: “የምናገረው እኔን በደምብ ይገልጸኛል ኳስን መልሶ የማግኘት/የማሸነፍ ተግባር በምቾት የማደርገው ነው አሁንም በዩናይትድ በትክክለኛው መንገድ እንደማደርገው አውቃለሁ::”

በዩናይትድ በኡጋርቴ መምጣት ምክንያት ቦታውን የማጣት ስጋት ያለበት በጨዋታዎች ስህተቶችን እየፈፀመ ያለው ብራዚላዊ ካሲሚሮ ነው አሰልጣኙ ሁለቱንም የማጫወት አማራጭ እስካልተጠቀሙ ድረስ::

ኡጋርቴ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን 98 ሸርተቴዎች ወርዷል በሊግ ኧ ከየትኛውም ተጫዋች በላይ:: በአማካይ 66% ፖዜሽን የነበረው ቡድን ውስጥ ከ 34 የፒኤስዤ የሊግ ጨዋታዎች በ 21 ብቻ ጨዋታ በጀመረበት:: የዩናይትድ ደጋፊ እንዲህ ያለውን ነገር በበለጠ ይጠብቃል:: ኡጋርቴ ከዲስትሮየርም በላይ እንደሆነ ይናገራል::

“ደጋፊዎች ያንን ቢጠብቁ ልክ ናቸው ምክንያቱም እንደ ህግ የማከብረው እንደ ትዕዛዝ የምፈፅመው ነው በሚሰጠኝ ሚና ደግሞም የአጨዋወቴ አንድ አካል ነው:: ነገር ግን ዲስትሮየር ብቻ አይደለሁም:: በኦልድ ትራፎርድ ያንን እስከማደርግ ጓጉቻለሁ::”

“ሁለገብ ተጫዋች እንደሆኩ ማሰብ እፈልጋለሁ ኳስን በማስጣል እና መልሶ ማግኘት በጣም ብቁ እንደሆንኩ ይሰማኛል ግን ደግሞ በፖዜሽንም ጥሩ መሆን እችላለሁ:: እርግጥ ነው የማሻሽላቸው ብዙ ነገሮች አሉ ነገር ግን በጣም ጥሩ በሆንኩበት ነገር የተሻለውን ከማድረግ በላይ ምን አለ?”

ኡጋርቴ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ከመምጣቱ አስቀድሞ ከፋኩንዶ ፔሊስትሪ ቡርኖ ፌርናንዴስ እና ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ጋር አውርቷል ዩናይትድ መድረሻው ይሆን እንደሆነ ለውሳኔ እንዲረዳው::

መድረሻው ዩናይትድ እንዲሆን ስላሳመነው ምክንያት ሲጠየቅ “በዋነኝነት እና ከሁሉ በላይ የክለቡ የላቀ ታሪክ ምክንያቱም ዩናይትድ እንዴት ያለ በጣም ትልቅ ግዙፍ ክለብ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን በዓለም ከምርጥ ክለቦች አንዱ:: ያነጋገርኳቸው የቡድኑ ተጫዋቾች ስለ ክለቡ ከባቢ ሲያወሩኝ ደስተኛ ነበርኩ:: በተለይ ከቡርኖ እና ሊቻ ጋር ብዙ አውርቻለሁ::

“ያለጥርጥር በዩናይትድ መሆን በኃላፊነት ለመጫወት እና ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ነው:: ወጣት ነኝ ለመማር ዝግጁ ነኝ:: የማሸነፍ ምኞት እና ፍላጎት አለኝ እነዚህን ነገሮች ለማሳካት ይህ ክለብ ተስማሚ ቦታ ነው::”

[ ሰላም ጎሳዬ ለፋስት መረጃ ከአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ]


5 comments

Ephraim Tamiru Efe September 7, 2024 - 7:04 am

Amanuel 😁

Reply
Samri Ethiopia September 7, 2024 - 7:07 am

ኧረ ተወኝ መንግስትም እንደዚህ የምርጫ ቅስቀሳ አርጎ አሻግራችኋለሁ ብሎ ከ6 አመት በኋላ ትላንት ተሻገሩ አለን ማንንም ማመን አልችልም ኡጋርቴንም😒

Reply
Mohe Muste September 7, 2024 - 7:07 am

በሳቅ😀😀😀

Reply
አሌክስ ቡንዬ አቡኪ September 7, 2024 - 7:09 am

እንዴ Fast Mereja ኩዋስ ትንተና ገባ:: እንዴት ሊሆን ቻለ

Reply
Meku Yemareyam Lij September 7, 2024 - 7:11 am

ሳይመጣ ወሬ አበዛ በቃ አይችልም ጀግና ገሎ ነው የሚፎክረው

Reply

Leave a Comment