ተመልከቱ የጠቢባን እጆች ምን መስራት እንደሚችሉ ፍቅር እስከ መቃብር መፅሃፍ የታተመበት የወረቀት ሽታ ሳይቀር ይታወሰኛል። በወቅቱ ሳነበው እጅግ አድካሚ መስሎ ቢታየኝም እንደወይን እያደር ግን እየጣመኝ ሄደ የገፁ ብዛት ግን ከአንድ ጊዜ በላይ እንዳልደግመው ነበር ያደረገኝ።
“ማር እስከ ጧፍ” በተሰኘው ዘፈኑ ቴዲ አፍሮ እጅግ ተራቆበት መጣ አለም ላይ ብትከታተል Huffman Coding ብትጠቀም LZ77 LZ78 ካሻህም BWT አያይ RLE አለም ላይ አሉ የተባሉትን ከጁስ መፍጫ እስከ እንጨት መደረቢያ የፈለከውን የኮምፒዩተር አልጎሪዝሞች ብትጠቀም ከቴዲ በስተቀር ይህንን ሚያክል መፅሃፍ በ6 ደቂቃ ሊተርክልህ አይችልም።
ተመልከት የጠቢባንን እጅ ፍቅር እስከመቃብር በፊልም ሊሰራ ነው ሲባል አይ አሁን በቃ ከመፅሃፉ በላይ እነዛ ገፀባህሪዎች መልካቸው ሊመጣብኝ ነው እያልኩ መሳቀቅ ጀመረኝ ገሚሱ ህዝብ ኧረ እንዳይበላሽ አለ። ሰውመሆን ግን እነዚህን ሁሉ ሃላፊነቶች ሳያሸሹት ጭራሽ የብእር ቀለም ምልክቱን ከኢቲቪ ጋር አሰፈረ። ይሰራ አይሰራ ቢያበቃለትም የሃሳብ ሙግቱ ግን ቀጠለ።
ፊልሙን ዛሬ ለውጤት በቅቶ ሳየው ሰውመሆን ከቴዲ ብዙ ነገሮችን ተውሶ አየው ተውሶም ግን አይመስለኝም ተመሳሳይ የጥበብ ከፍታ ላይ ሲደርሱ ጥበብን የሚመለከቱበት የአይናቸው ብሌን በእኩሌታ ሰፍቶ መሰለኝ።
ቴዲአፍሮ “ማር እስከ ጧፍ” Winrar ሳይጠቀም አፕሊኬሽን ሳይጭን AI እንኳ ቢጠቀም ማያገኝለትን የታሪክ መጠቅለያ ምስሉን ሲቀርፅ የገፀ ባህሪዎቹ አለባበስ ፣ የቅዳሴ ስነስርአቱ ፣ የምስሉ ልዩ ቀለም ( ቀይ Effect መጠቀሙ ይህንን አይነት Cinematography ያየነው “የእግር እሳት” የተሰኘው ተከታታይ ድራማ ላይ ብቻ ነበር) ሁሉም ነገሮቹ የመፅሃፉን ገፅ በገፅ ያስታውሰናል።
ሰውመሆን ብዙ ለአይን የሚማርኩ ለጆሮ የሚስቡ ከራሳችን አንደበት እንኳ ስንመሰክርለት ልባችንን በሀሴት የሚያስሞላ ስራዎችን ቀድሞ የሰራ ሲሆን ይሄኛውን ፊልም ግን ለታሪክ የሚቀመጥለት Masterpiece የምንለው አይነት ነው የሚሆነው። 50 ሚሊዮን ብር የወጣበትን ስራውን እንዲሁ በከንቱ አላደከመውም።
አስበው ሰውየው ትወና ብቃት ብቻ አላየም አካባቢውን የሚመጥን ሰውም ይፈልግ ነበር የወቅቱን ቀለምም ያለውን ሰው ጭምር በፊልሞቻቸው እጃችንን በአድናቆት ያስላጡን ሰዎችን አላመጣም አዳዲስ ሰዎችን አስገብቶ እንዲፈኩ አደረገ።
ለፍቅር እስከመቃብር ለዘላለማዊ ለሚፈጠርብን ምስል እጅግ ተጠንቅቆ እንደሰራው ያስታውቃል አስበው ሁለት ጣትህን ከተህ በቲያትሮቿ ያጨበጨብክላት መስከረም አበራ ብትሰራው ኖሮ “በስንቱ” የተሰኘው ተከታታይ ድራማ ላይ ሂሩትን ባየን ቁጥር ፍቅሯን በዛብህን ወይስ በስንቱን እያሰብን እንወዘጋገብ። ታዋቂ አንጋፋ በብዙ ስራዎቻቸው የምናከብራቸውን የምናደንቃቸውን ስክሪናችንን አምስት ጊዜ ብንገልጥ ሁለቴ ማናጣቸውን አርቲስቶች አለመጠቀሙ ሰውመሆንን ከተሰቀለበት የጥበብ ደመና ላይ በዝናብ መልክ እንኳ እንዳይወርድ ያደርጉታል።
መፅሃፉን ወደን አንብበን በቴዲ ዘፈን እንዳይሰለቸን ሆኖ በዛብህም ሰብለም በናፈቁን ቁጥር በየስድስት ደቂቃው እየደጋገምን ውስጣችንን አስደስተን ሳንጨርስ የማንከፋበት የማንደበርበትን አስገራሚ የጥበብ ስራህን ስላበረከትክልን ከዚህ የበለጠ ከፍታ ላይ እንዳይህ ተመኘው። ከዘመናት በውሃላ በሁሉም ነገሩ ፅድት ያለ ፍፁማዊ ፊልም ተገኘ ፍቅር እስከ መቃብር!!!
[ ተፃፈ በሄኖክ አረጋ በፋስት መረጃ ]

10 comments
A ጦ D
ሄኖክ አረጋ ፕሮፌሰር 😍
”ፕሮፌሰር” በል አንተ😑
በበሁሉነገሩ የተዋጣለት ሆኖ ሳለ የሰ ብለን ገፀባህሪ ቅንድቧን ተቀንድባና ፀጉሯን ተተኩሳ መቅረቧ ለምን አስፈለገ
ሌላውማ ለጆሮ ፍትህ ያስጠይቃሉ
𝑠𝑜ሚክ ይችላል
የፍቅር እስከመቃብር መቼቱ ጐጃም እንደሆነ ይታወቃል።መፅሐፉ ሁለት ጋዜ አንብቤዋለሁ።
የዛ ሰፈር ሴቶች ለፍቅር ሟች መስለውኝ አንድ ጐጃሜ በጠና አፈቀርኩ።እውነቱ ግን ፍቅሬን እንደድርሰቱ ምናባዊ አደረገችብኝ።
ሙስሊም ሳትሆኑ ሞት እዳይቀድማቹ
SPECIALLY
የምናውቃቸውን ተዋናዮች አለመጠቀሙ ሪል ታሪክ እያን እንዲመስለን አድርጎታል።
ታዋቂ ተዋናዮች ቢሆኑ ፊልም እንደሆነ ግማሽ ልባችን ስለሚያውቅ ሙሉ ስሜት አይሰጥም።
እኔ መጽሃፉን አላነበብኩትም ግን በቃ ፊልሙ ከ ካስቲንግ ጀምሮ እስከ የታሪክ ፍሎው 1ኛ ነው አንዱን ክፍል 10 ጊዜ ይሆናል ያየውት እንደው ከነዛ መናጢ ፊልሞች ገላገልከን ቶሎ ቶሎ ብቻ ልቀቁልን