banner

«በብርድ ጎዳና ላይ እያደርኩ ወደ ልምምድ እሄድ ነበር፤ በረንዳ ሳድር አይቶኝ ቤት የሰራልኝ ሰው አለ…. » እስራኤል መስፍ

«በብርድ ጎዳና ላይ እያደርኩ ወደ ልምምድ እሄድ ነበር፤ በረንዳ ሳድር አይቶኝ ቤት የሰራልኝ ሰው አለ…. » እስራኤል መስፍን

በቅርቡ አሜሪካ ላይ ለተደረገው የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ወደቦታው ከተጓዙ ተጫዋቾች መካከል የኢትዮጵያ ቡናው ግብጠባቂ እስራኤል መስፍን አንዱ ነው። በእግርኳስ ህይወቱ ስላለፈበት መንገድ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ. ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ቆይታ አድርጓል።

👉ስለአሜሪካው ጉዞ እና “ቀርቷል” ስለመባሉ

«በጣም አሪፍ ነበር ደስይል ነበር ሀገሩንም ጎብኝተናል ብዙም ባይባል መታየት ያለባቸውን ቦታዎች አይተናል ። ጠፋ የተባልኩበት ምክንያት ከጓደኞቼ ጋር ገበያ ወጥተን ዕቃ ለመግዛት ነበር በድንገት ክላስ ሲፈተሽ እኔ አልነበርኩም ከዛ ራሴው መጥቼ አለሁ ብያለሁ። የተሻለ ህይወትን የሚጠላ የለም ሆኖም በገንዘቡ ብቻ ሳይሆን በስራው ራስን ማሳየት ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ »

👉እስራኤል ትውልዱ አሰበ ተፈሪ ጭሮ ዕድገቱ ጎፋ መብራት ሀይል አካባቢ እንደሆነ ይናገራል። በኤሌክትሪክ ሲ ቡድን ኒያላ እና ኢትዮጵያ መድንም ተጫውቷል። (በመንገዱ ላይ የነበሩ አሰልጣኞችን ስም ጠቅሶ አመስግኗል)

አሁን ወደሚገኝበት ኢትዮጵያ ቡና የገባበት አጋጣሚ እንደሚለይ ይናገራል።

« 3 ግብጠባቂዎች ተይዘው ሞልቶ ነበር አጋጣሚ ግን አሰልጣኝ ዕድሉ ደረጄ አይቶኝ አራተኛ አድርጎ ያዘኝ በመሀል አንድ ሰው ቀረ እና ቀጠልኩ። »

👉ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኃላ ያለፈበት መንገድን በተመለከተ??

«በጣም ህፃን ልጅ እያለሁ ነው ወደ አዲስ አበባ የመጣሁት ዘመድም የለኝም። እናም ደሞዙ የሚበቃኝ ስላልነበር ቤት መከራየት አልቻልኩም በብርድ ጎዳና ላይ እያደርኩ ነበር ወደ ልምምድ የምሄደው በተስፋ ቡድኑ ያለው መንገዴ እንደዛ ነበር። አሁን ወደኋላ መለስ ብዬ ሳስበው እምባዬ ይመጣል። እስክንድር የተባለ ሰው በረንዳ ሳድር አይቶኝ ዘበኞች የሚተኙበትን ቤት ሰራልኝ። ጎፋ መብራት ሀይል አካባቢ ያሉ ሰዎች መልካም ናቸው። የትም ክለብ ለተስፋ ቡድን ምግብ የሚሰጠው አንዴ ነበር ከዛ ውጪ የነበረው ያስጨንቀኝ ነበር።

በ2009 ነው ወደ ዋናው ቡድን ያደኩት እንቅልፍ መተኛትም መረጋጋትም የጀመርኩት ከዚህ በኃላ ነው ካምፕም ገባሁ ምግብም እንደልብ አገኘሁ። ከባድ ጊዜ ነበር ከብርድ እየተነሳሁ ነበር ወደ ልምምድ የምሄደው። አሁን ሁሉም አልፏል እግዚአብሄር ይመስገን» ሲል ይናገራል።

#እስራኤል በቆይታው ስለፕሪምየር ሊጉ አስተያየቱን ሰጥቶ ፉክክሩ ከባድ እንደሚሆን ግምቱን አስቀምጧል።

Via: ኑራ ኢማም

3 comments

Hilwa Al Mektum September 18, 2024 - 5:12 pm

አለሁ ብለህ መጣህ? ክክክክክክ

Reply
Solo Nick September 18, 2024 - 5:14 pm

እና ተመለሰ ነው ምትሉኝ ወደ ጎዳና 😂

Reply
Bereket Asfaw September 18, 2024 - 5:16 pm

ለምን መጣህ አልልህም። አመስጋኝነትህና ፈሪሀ እግዚአብሄር እንዳለህ ንግግር ይናገራል።መልካም የስራ ዘመን ማህበሩ ሚኮራብህ ውዱ አበላችን

Reply

Leave a Comment