banner

«ጉርሻ ሀብ» የተሰኘ የሚከፍል ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ ሆነ።

#FastMereja
ጉርሻ ሀብ የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች እና የይዘት ፈጣሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የማስታወቂያ ገቢ መጋራትን ብቸኛ አማራጭነት በማለፍ ፣ የአድናቆት ጉርሻ ከመቀበል ጀምሮ፣ በቋሚ ተመልካች ሜምበርሺፕ ምዝገባ እና በዲጂታል ይዘት ሽያጭ ክህሎታቸውን አይነተኛ ቋሚ ገቢ ማድረግ የሚያስችላቸው ቀጥተኛ የይዘት ገቢ መፍጠሪያ የድህረ-ገፅ መተግበሪያ መሆኑ የመተግበሪያ አበልፃጊዎች ዛሬ መስከረም 9/2017 ዓ.ም በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

አለም አቀፋዊ ግዙፍ የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች በኢትዮጵያ የሚኖሩ ተጠቃሚዎቻቸውን ያማከለ የይዘት ፈጣሪዎች እና አድናቂዎቻቸውን የድጋፍ እና የሸልማት ማጋራት መስተጋብር የሚያሳልጥ የክፍያ ስርአት ስላላዘጋጁ የተፈጠረ ትልቅ ክፍተት አለ ያሉት የጉርሻ ሀብ አበልፃጊዎች በዚህም የተነሳ የሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያ እምርታ እና የተሰጥኦ ዝመና በአሉታዊ ተፅእኖዎች ስር ሲወድቅ ይስተዋላል ብለዋል።

በጉርሻ ሀብ የሚገኙ ፊውቸሮች Donations፣ Memberships፣ Digital Extras Shop፣ Crowdfunding፣ Partnerships ሲሆኑ የክፍያ ሂደቱም በቻፓ (Chapa) የክፍያ አማራጭ እንደሚከፈል ነው የተገለፀው።





2 comments

Azma Menzo September 19, 2024 - 12:22 pm

የምናውቀው ጉርሻ ከሆነ እሰዮ🙏

Reply
Afework Eyayu September 19, 2024 - 12:25 pm

የመጀመሪያዎቹ ሁለት አንቀፆች በጣም የታጨቀ ሀሳብ ስለያዙ ያላችሁት አልገባኝም። ቀጣዮቹ ሁለት አንቀፆች እንዴት ሁለት አረፍተ ነገር ብቻ ይሆናሉ??? አልገባኝም!!

ጉርሻ ሀብ የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች እና የይዘት ፈጣሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የማስታወቂያ ገቢ መጋራትን ብቸኛ አማራጭነት በማለፍ ፣ የአድናቆት ጉርሻ ከመቀበል ጀምሮ፣ በቋሚ ተመልካች ሜምበርሺፕ ምዝገባ እና በዲጂታል ይዘት ሽያጭ ክህሎታቸውን አይነተኛ ቋሚ ገቢ ማድረግ የሚያስችላቸው ቀጥተኛ የይዘት ገቢ መፍጠሪያ የድህረ-ገፅ መተግበሪያ መሆኑ የመተግበሪያ አበልፃጊዎች ዛሬ መስከረም 9/2017 ዓ.ም በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

አለም አቀፋዊ ግዙፍ የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች በኢትዮጵያ የሚኖሩ ተጠቃሚዎቻቸውን ያማከለ የይዘት ፈጣሪዎች እና አድናቂዎቻቸውን የድጋፍ እና የሸልማት ማጋራት መስተጋብር የሚያሳልጥ የክፍያ ስርአት ስላላዘጋጁ የተፈጠረ ትልቅ ክፍተት አለ ያሉት የጉርሻ ሀብ አበልፃጊዎች በዚህም የተነሳ የሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያ እምርታ እና የተሰጥኦ ዝመና በአሉታዊ ተፅእኖዎች ስር ሲወድቅ ይስተዋላል ብለዋል።

Reply

Leave a Comment