0
በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ስሙ መናኸሪያ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ትናንት ምሽት 05:00 ገደማ በተነሳ የሳት ቃጠሎ 31 የንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለጸ።
ሱቆቹ የአልባሳት ሸቀጣሸቀጥ ኤሌክትሮኒክስ ማተሚያ ቤትንና የመሳሰሉትን ያካተቱ ሲሆን ባለቤትነታቸው የለፍቶ አዳሪ ወጣቶች መሆናቸው ተነግሯል።
የቃጠሎውን መንስኤ አጠቃላይ የወደመውን ንብረት ግምትና ወደፊት ሰለሚወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ከመንግስትና ከንግዱ ማህበረሰብ የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ መረጃዎችን በማጠናቀር ላይ በመሆኑ ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
ቃጠሎው ወደሌሎች ንግድ ቤቶችና ድርጅቶች ተስፋፍቶ የበለጠ ውድመት እንዳያደርስ የአከባቢው ነዋሪዎች የጸጥታ አካላት የውሃ አገልግሎት ተቋማት ባለሙያዎችና ውሃ አቅራቢ ግለሰቦች ሚናቸው ትልቅ ነበር ተብሏል።
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1





2 comments
የማራቶን ሯጭ ፈሪው ፋኖ ነው ያቃጠለው ።
የግብፅ እጅ አለበት