banner

በጋምቤላ ክልል በጂካዎ ወረዳ ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ

በጋምቤላ ክልል በጂካዎ ወረዳ ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡጉላ ኡጁሉ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን በመጓዝ ላይ የነበረ አምቡላንስ በጂካዎ ወረዳ የባሮ ወንዝ ጊዜያዊ ድልድይን ጥሶ በወንዝ ውስጥ በመግባቱ ነው ብለዋል።

የ7 ሰዎች ህይወት ወዲያው ማለፉን የገለፁት ኮሚሽነሩ ከሟቾቹ መካከል የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።

የሟቾቹ አስክሬን ለማውጣት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

በአደጋው ሌሎች 7 ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና በመከታተል ላይ መሆናቸውንም ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ኮሚሽነር ኡጉላ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ሊያሽከረክሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

4 comments

Kalkidan Dawit September 25, 2024 - 10:40 am

ፈጣሪ ወጥቶ ከመቅረት ይሰውረን 🙏

Reply
Atnafu Alemayehu September 25, 2024 - 10:43 am

አምቡላንስ ስንት ሰዉ ጭኖ ነዉ??ነብስ ይማር

Reply
Senty Negn September 25, 2024 - 10:48 am

እፍፍ የሞት ዜና በየቀኑ መስማት ይደክማል ፈጣሪ በቃ ይበለን ነብሳችሁን ይማረዉ

Reply
ማህደር የሽወንድ September 25, 2024 - 10:51 am

አንድ አንቡላንስ ውስጥ 14 ሰው🙄

Reply

Leave a Comment