#FastMereja
እዝነት አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ መስከረም 26/2017 ዓ.ም የአለም አቀፍ የሲፒ ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ የእግር ጉዞ ሊያዘጋጅ የነበረ ቢሆንም በዚህ ሰሞን ከሚከበረው ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እንዲሁም በምልአተ ህዝብ የሚከበር አመታዊ ክብረ በአል (እሬቻ) ጋር ስለተገጣጠመበት መርሃ ግብሩን የሚያረደርግበትን ቀን ወደ ጥቅምት 03/2017 ዓም ተላልፎል ።
የድርጅቱ መሰራች እና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘቢባ አህመድ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስተላለፉት ቀን ለውጡን ያረግንበት ዋና አላማ የህዝቡን ትኩረት እና ድጋፍ በይበልጥ ለማግኘት፣ እንደ እቅዳችን ብዙ ህዝብ ያካተተ ሆኖ ተደራሽነቱ ከፍ እንዲል፤ ደስ ብሎን ተቀብለን ለአንድ ሳምንት አስተላልፈነዋል ብለውዋል፡፡ እንዲሁም ቀኑን የቀየርነው አምነንበት ቢሆንም ቀደመው ቲሽርት ለገዙ ተሳታፊዎችም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የዓለም የሰረብራል ፓልሲ ጉዳተኞች ቀንን ተንተርሶ የሚዘጋጀው መርሃግብር በ አዲስ አበባ ከተማ ጥቅምት 03/2017 ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ድረስ መነሻውን አድዋ 00 _መዳረሻውን ኩባ ፓርክ በማድረግ የእግር ጉዞ ሲሆን፤ በዕለቱ እዝነት ስለጉዳቱና ጉዳተኛ ህፃናቱ በሚታገዙበት ሁኔታ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን ለማከናወን ዝግጅቱን ሁሉ አጠናቆ ዕለቱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
ተሳታፊውንም ቲሽርቶቹን በቀላሉ በመግዛት ተሳታፊ እንዲሆኑ እና አጋርነታችውን እንዲያሳዩ ጋብዘዋል በፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ኣካላት፣ ኣጋር ድርጅቶች ፣ተጋባዥ እንግዶች ና የሀይማኖት አባቶችን ጨምሮ ከ 5000 በላይ ተሳታፊዎች በአንድ ይሰበስባሉ። እንዲሁም አዝናኝ ጨዋታዎች፣ የተለያዩ ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮች እና መሰል ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል።


