📌 ለዲላ ማረሚያ ቤት የመፅሐፍት ድጋፍ ተደረገ
#FastMereja
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከጌዲዮ ዞን ትምህርት መምሪያ እና ከዲላ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ ዛሬ መስከረም 24/2017 ዓ.ም ተከፍቷል።
የንባብ ሳምንት መርኃ ግብሩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት የዲላ ከተማ ከንቲባ አቶ ዳንኤል ሽፈራው ኢንተርኔት ንባብ ችል እንዲባል አድርጎታል፣ ንባብ በጥልቀት የማሰብ ችሎታን ያዳብራል ያሉ ሲሆን አሁን ያለው ትውልድ የንባብ ባህሉን ማዳበር ይጠበቅበታል ብለው መልካም የንባብ ሳምንት እንዲሆን ተመኝቷል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኤልያስ አለሙ ባደረጉት ንግግር ማንበብ የሚረዳ እና የሚያስተውል ትውልድ ለመገንባት ይረዳል እናንብብ ሲሉ መልዕክት አስተላልፏል።
86ኛ አመት የሞላው የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ሲቋቋም በሀገሪቱ የዩኒቨርሲቲ ተቋማት አልነበሩም ያሉት የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት /ወመዘክር/ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አባተ ካሳሁን ተቋሙ መሰረቱ ንባብ የእውቀት መሰረት እንደሆነ አሳይቷል ብሏል።
በዲላ ማረሚያ ቤት በመገኘት 200 መፅሐፍቶችን ለማረሚያ ቤቱ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት /ወመዘክር/ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በረድኤት ተረፈ ግጥም፣ መምህር መሰረት አበጀ ንባብና ህይወት በሚል ርዕስ ገለጻ ተደርጓል፣ ደራሲ ዘነበ ወላ፣ ደራሲ ሊዲያ ተስፋዬ፣ ደራሲና ሃያሲ ገዛኸኝ ሀብቴ በማረሚያ ቤት በመገኘት በንባብ ዙሪያ ለታራሚዎች የህይወት ስንቅ የሚሆናቸውን ንግግር እና ገለፃ አድርጓል።
በዲላ ከተማ የተዘጋጀ የንባብ ሳምንት፣ ቡክፌር፣ ኤግዚቢሽን እና የፓናል ውይይት እስከ መስከረም 28/2017 ዓ.ም እንደሚቆይ ተገልጿል።





1 comment
ጌዲዮ ሳይሆን #ጌዴኦ በምል ይስተካከል!