banner

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ታላላቅ ደራሲዎች በተገኙበት የወጣቶች የስነ ጽሑፍ ምሽት ተካሄደ።

#FastMereja
“የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል በዲላ ከተማ እየተካሄደ ባለው የንባብ ሳምንት መርሃ ግብር በዛሬው የመስከረም 25/2017 ዓ.ም ውሎ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሀገራችን ታላላቅ ደራሲዎች በተገኙበት የስነ ፅሁፍ ምሽት ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ ደራሲ ዘነበ ወላ፣ ደራሲ ይታገሱ ጌትነት፣ ደራሲና ሃያሲ ገዛኸኝ ሀብቴ፣ ገጣሚ ረድኤት ተረፈ፣ ደራሲ ሊዲያ ተስፋዬ፣ ደራሲ አንለይ ጥላሁን ስለ ንባብ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን ተሳታፊ ተማሪዎችም በመድረኩ ላይ የግጥም ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።

ዶ/ር አለማየሁ አካሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው የዛሬው አይነት የስነ ፅሁፍ መርሃ ግብሮች በዩኒቨርሲቲው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው ፕሮግራሙ ለተማሪዎች የንባብ ባህልን ለማዳበር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከጌዲዮ ዞን ትምህርት መምሪያና ከዲላ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የንባብ ሳምንት አካል የሆነው የዲላ ከተማ ተማሪዎች በተገኙበት የንባብ ክበባት ምስረታ መርሐግብር ተከናውናል።





2 comments

Beki B Six Yahama October 5, 2024 - 7:11 pm

ተዉ ግን ትዝብት ነዉ ጌዲዮ አይደለም
#ጌዴኦ ነው እንጅ!!

Reply
YS Man October 5, 2024 - 7:12 pm

ለምን አልጠራችሁኝም ታዋቂ መሆን ነበረብኝ?

Reply

Leave a Comment