በጋምቤላ ክልል በአሁኑ ወቅት ኮንዶም አግባብ ባልሆነ ዋጋ ለሽያጭ እየቀረበ እንደሚገኝ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል::
በቢሮው የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድምአገኘሁ በላይነህ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በክልሉ ያለው የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ከፍተኛ ነው:: በአሁኑ ወቅት የስርጭት ምጣኔ 3 ነጥብ 24 መድረሱን ገልፀው በክልሉ እንደ ባህል ሆኖ የሚቆጠረው የውርስ ጋብቻ መበራከት እንዲሁም የተለያዮ ባህላዊ ጨዋታዎች ላይ የሚደረግ ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት መኖር በሽታው እንዲስፋፋ ማድረጋቸውን ተናግረዋል::
በበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ሴቶችና በወጣትነት እድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች ናቸው። በክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመከላከል የሚረዳው የኮንዶም ዋጋ መናር ሰዎች እራሳቸውን ከበሽታው ለመከላከል እንቅፋት እንደሆነባቸው ተገልጿል::
በክልሉ በአሁኑ ወቅት በነፃ በሚታደለው ሆነ በበርካታ የመሸጫ ቦታዎች በ50 ብር ለሽያጭ ሲቀርብ የነበረው ኮንዶም እስከ 150 ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሚገኝ ባደረግኩት ምልከታ አረጋግጫለሁ ሲል ቢሮው አስታውቃል:: ለጉዳዮ መፍትሄ ለማምጣት ከሚመለከታጨው አካላት ጋር በመሆን ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ቢሮው ገልጿል::
አግባብ ባልሆኑ ዋጋ ኮንዶምን ለሽያጭ በሚያቀርቡ አካላት ላይም የማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ከድርጊታቸው በማይመለሱ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተጠቁማል።
Via: ዳጉ ጆርናል

10 comments
እና Short ስንት ነው😳💔
ለሀምሳ ሰዉ ለመግዛት ቃል እገባለሁ ✋
ሸምሱ ሰምተው ይሁን
ሾርት ስንት ሊሆን ነው ኮንዶሙ እንዲ ከሆነ
ትንሽ ቆይቶ ደግሞ መንግስት breaking news “በህገወጥ ምንገድ ሲዘዋወር የነበረ ኮንዶም በቀጥጥር ስር ዋለ”🥺
ስለዚ በጋምቤላ ክልል ኮንዶም ነጋዴ መሆን ያዋጣል 🤔
ጋቤላ ክልል ምን እየተካሄደ ነው ያለው🤔 የሚሰማው ነበር ወጣ እያለብኝ ነው
እኛ ሳናውቀው የ ኤችአይቪ መዲሃኒት ሆነ እንዴ 😳😳😳
አቤት ዘንድሮ ያልጨመረ ነገር የለም🤔🤗
ጋምቤላዎች ኑ እስት