banner

የራይድ ቤተሰቦች የቤት ባለቤት ሊሆኑ ነው።

#FastMereja
ኦቪድ ሪል እስቴት፣ ራይድ ትራንስፖርት (Hybrid Designs PLC) እና ሰዋሰው መልቲሚዲያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስራ ውል ሰምምነት ተፈራረሙ።

ኦቪድ ሪል እስቴት ለራይድ ትራንስፖርት፣ በስሩ ለሚገኙ ተቋማት እና ራይድ ቤተሰብ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ የዋጋ ቅናሽ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን በአጠቃላይ በኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የራይድ መንደር ለመገንባት ተሰማምቷል።

ሀይብሪድ ዲዛይንሰ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ራይድ) ቤተሰቦቹን ተጠቃሚ ባደረገ መልኩ ኦቪድ ሪል እስቴት ለአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ለሚገኙ ደንበኞቹ ለሚያቀርበው የቤት ሽያጭ አገልግሎት ገበያውን በማስተዋወቅ ይስራል፣ ያስተባብራል ተብሏል።

በሰዋሰው መልቲ ሚዲያ በኩል የሚገኙ አንጋፋና ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች፣ አርቲስቶች ዲጄዎች እና ከያኒያንን በተመጣጣኝ ዋጋ እና በልዩ ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ቅናሽ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት የተመቻቸላቸው ሲሆን ባለሙያዎቹም ኦቪድ ሪል እስቴት የሚያቀርባቸውን የቤት ሽያጭ ከአጋሮቹ ጋር ያከናውናል ተብሏል።

📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ





3 comments

Yeabsira Berhanu October 10, 2024 - 9:06 am

ዘመናዊ ባርነት

Reply
ሄርሞን ልዑል October 10, 2024 - 9:08 am

ያለህን ትከፍላለህ ሊብሬ ትጨምራለህ ከዛ ቤተለን ለ10 አመታት ትጠብቃለህ ቤቱ ስለመኖሩንኳን ሳታቅ በየወሩ በሽዎች ለአቢይ አህመድ ድርጂት(ኦቪድ)መቆጠብም አለብህ በሂደቱ የራይድ ስልታዊ ባሪያ ትሆናለህ መለትኖ😃የታከለ ውማ ውሽማግን እልቻልሽም😁

Reply
Medi Yeheyis October 10, 2024 - 9:16 am

ጌጡ ግን አቃጣሪ ነህ 🙄

Reply

Leave a Comment