0
#FastMereja I የኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር በኢትዮጵያ ቱሪዝም ላይ የበኩላቸውን አስተዋጾ ላደረጉና እያደረጉ ላሉ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ሰጠ።
ማህበሩ የዓለምን ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ” ቱሪዝምና ሰላም ” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሽልማትን በአዲስ አበባ ሙዚየም አካሄደ።
የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው በዚህ የሽልማት ስነስርዓት ላይ ለአራት ተቀሟትና ለስድስት ግለሰቦች እውቅና ሰቷል።
በሽልማት ስነስርዓቱ የተሸለሙት አራቱ ተቋሟት
📌 የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፣
📌 ቱሪዝም ማስልጠኛ ኢኒስቲትዩት ፣
📌 ኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች
📌 አንድነት ፓርክ ናቸው።
ማህበሩ ከአራቱ ተቋሟት በተጨማሪ ለስድስት ባለሙያዎች ሽልማት ሰቷል።
📌 ጋዜጠኛ ፀሐይ ተፋረደኝ ፣
📌 ጋዜጠኛ ሄኖክ ያሬድ ፈንታ ፣
📌 ፎቶግራፈር አንቶኒዮ ፈዮርንቴ ፣
📌 የቱሪዝም ባለሙያ ቴዎድሮስ ደርበው ፣
📌 ፎቶግራፈር ህሊና ታፈሰ
📌 አርቲስት ኪሮስ ኃ\ ስላሴ ናቸው።
ይህ የቱሪዝም ሽልማት በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ዓመታዊ የሽልማት ስነስርዓት ሆኖ እንደሚቀጥል በመድረኩ ተገልጿል።




