banner

ሰሞኑን በሀገራችን የተፈፀመ አሳፋሪ ድርጊት እንገራችሁ። #ሼር

📌 “ባለቤትሽ ጋር ለምን አልመለስም አልሽ በማለት ልጆቿና ህዝብ ፊት በባለቤቷ እንድትገረፍ የተወሰነባት የልጆች እናት”

ጉዳዩ እንዲህ ነው። ወ/ሮ ኩሹ ቦናያ ምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ቃቀሎ ቀበሌ ነዋሪ ናት። ወ/ሮ ኩሹ ከአቶ ገልገሎ ዋሪዮ ጋር ትዳር ከመሰረቱ 12 አመታት አስቆጥሯል ሶስት ልጆም ወልዷል።

ፋስት መረጃ ከቤተሰብ የደረሰው መረጃ ወ/ሮ ኩሹ ሶስተኛ ልጃቸውን ነፍስጡር ሆነው ባለቤታቸው የሀገር መከላከያ ተቀላቅለው ለግዳጅ 4 አመት ሌላ ቦታ ቆይቷል።

አራት አመታትን ሶስት ልጆችን ብቻቸውን ያሳደጉት ወ/ሮ ኩሹ ከአራት አመታት በኋላ ባለቤታቸው ከመከላከያ ተሸኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ጉዳዩን ለፋስት መረጃ ያስረዱት የቤተሰብ አባል አቶ ገለግሎ ሲመለሱ የተለያዩ ሱሶችን ስለለመዱ ትዳሩ እንደቀድሞ ሰላማዊ ሊሆን አልቻለም ጭቅጭቅ እና ግጭት ተከሰተ ይላሉ።

ወ/ሮ ኩሹ ትዳራቸው እንዳይፈርስ በተደጋጋሚ በሽማግሌ ብታስመክርም ባለቤቷ ሊስተካከል ስላልቻለ ከአቅሟ በላይ ሲሆን ወደ ቤተሰቦቿ ትሄዳለች።

ይህን ጊዜ ባል ሀገር ሽማግሌዎችን በመላክ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ያስጠይቃል፣ ወ/ሮ ኩሹ የእኔ ጉዳት አልታየም በፍፁም አልመስም በማለት የሽማግሌዎቹን ጥያቄ ውድቅ ታደርጋለች።

ሽማግሌዎቹም የምንልሽን ስሜ ቶሎ ወደ ቤትሽ ተመለሺ ካልሆነ ቅጣት እንጥልብሻለን በማለት ሲያጠነቅቋት እንደቆዩ ተበዳይ ትናገራለች።

በእምቢታ የፀናችው ወ/ሮ ኩሹ በሽማግሌዎቹ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባት በገመድ ከግንድ ጋር ታስራ በልጆቿ እና በህዝብ ፊት በባለቤቷ እንድትገረፍ ተደረገ።

ስትገረፍ የሚያሳየው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ ህዝቡ ቁጣውን መግለፅ ጀመረ። (ቪዲዮ በቴሌግራም ገፃችን ላይ ይገኛል)።

ይህን ውሳኔ አስተላልፏል የተባሉት ሽማግሌዎች ጃርሶ ቦሩ፣ ገልገሎ ጃተኒ፣ ዲዳ ዋሌ፣ ዲዳ ጃተኒ፣ አለካ ጃርሶ፣ ባርጪ ኢያ፣ ዲባ ጎሊቻ የተባሉ ሲሆኑ ፋስት መረጃ በደረሰው መረጃ እነዚህ ሽማግሌ የተባሉ ግለሰቦች 5 ቀን ታስረው በዋስትና መለቀቃቸውን ሰምተናል።

እጅግ አሳፋሪ ድርጊት የተባለው ቪዲዮ እዚህ ፖስት ማድረግ ስለማይፈቀድ በቴሌግራም ገፃችን ላይ ያገኙታል።

📌 https://t.me/fastmereja
📌 https://t.me/fastmereja




10 comments

Titi Fam October 18, 2024 - 4:17 pm

መቼም የማይሰለጥን ህዝብ😒

Reply
Keros Gezahegn Keros October 18, 2024 - 4:19 pm

እውነተኛ ፍትሕ ያለው ፈጣሪ ጋር ብቻ ነው

Reply
Rafael Gashaye Ale October 18, 2024 - 4:19 pm

አሁን እሄ መከላከያ ቆይቶል ይባላል? ሽማግሎችስ አንዴ ታውረዋል። መከላከያ እንደዚህ ነው ስነመግባራችሁ ።

Reply
Belew Kinfe October 18, 2024 - 4:21 pm

አሳፋሪና ሽምግልና እንድንጠላ ያደርጉናል

Reply
Filmon Filari October 18, 2024 - 4:21 pm

ኣይ መለስ ዜናዊ …..

Reply
Teddy Demeke October 18, 2024 - 4:23 pm

እንዲህ አይነት ጠሚ ነው የገጠመን

Reply
Muller Mule October 18, 2024 - 4:23 pm

Yasazenal. Ye Abiy mekelakeya serat yemibal yelewem yemenelew eko lezhi new. Yasazenal

Reply
Kidest Dejene October 18, 2024 - 4:24 pm

የደናቁርት መንጋ😡

Reply
Yo Yo October 18, 2024 - 4:24 pm

መቼ ነው ግን ሴት ልጅ ላይ የሚደርሰው ጥቃት የሚቆመው 🥺

Reply
Nīmőňá Bedasa October 18, 2024 - 4:26 pm

Zufan ስጀመር በሰው ትዳር ውስጥ የምን ሽማግሌ ነው የእሷን ኑሮ እነሱ ናቸው እንዴ የሚኖሩላት

Reply

Leave a Comment