0
በአዲስ አበባ ሳሪስ ቀይ አፈር አካባቢ የ20 ዓመት ወጣት የሆነው እንዳለ ሀብቴ ከመኖሪያ ቤት ተጠርቶ ከወጣ በኃላ በደረሰበት የጩቤ ጥቃት ህይወቱ አልፎ መገኘቱን እህቱ አለም ሀብቴ ለዳጉ ጆርናል ተናግራለች።
ወጣቱ ከወላጅ እናቱ ጋር የሚኖር ሲሆን ኳስ ከመጫወት እንዲሁም በቀይ አፈር አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን በመታዘዝ በመልካም ስብዕናው ይታወቃል።
የወጣቱ አሟሟት እና ከዚህ ጀርባ እጃቸው ያሉበት ሰዎች ፍትህ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ስትል እህቱ አለም ሀብቴ ጨምራ ለዳጉ ጆርናል ተናግራለች። ስርዓተ ቀብሩ ነገ ጥቅምት 10/2017 ይፈፀማል።
Via: ዳጉ ጆርናል


10 comments
እንደውም ፍርዱ ቆየ ተንቀጥቅጦ በጨረሰን 😭😭
አሁን አሁን እንደዚህ አይነት ዜናዎች መቅረብ ቢቆም ጥሩ ይመስለኛል ለወንጀለኞች ትምህርት እየሰጠ እና ነገሮች እየተባባሱ መጡ እንጂ ምንም እያተረፍን አይደለም።
RIP
በናታችሁ Fast mereja ሞትን አቅልላችሁ አትዘግቡ ትንሽ ለቤተሰብ ይከብዳል።
ፈጣሪ ሀገራችንን እና ህዝቦቻችንን ይጠብቅልን። የሞቱትንም ነፍሳቸውን ይማርልን🙏🙏
ሰዉ እራሱ ከፍቶ፤ ጨካኝ አረመኔ አውሬ ሆኖ መልሶ ደግሞ ጣቱን ወደ ሌላ ይቀስራል። ሁላችንም በእውነተኛ ንስሐ ወደ ፈጣሪ ብንመለስ ይሻለናል። ገዳይም ተገዳይም ሁለቱም የእኛ ልጆች የአብራካችን ክፋይ ናቸው። በፈሪሃ እግዚአብሔር አንጸን ብናሳድጋቸው፣ በስርዓት ተኮትኩተው ቢያድጉ ይሄ ባልሆነ። ያልዘራነውን ለማጨድ የምንሞክረው የእኛ የሁላችንም ጥፋት ነው። ልጆቻችን አፍ መፍቻቸው እናትህን እንዲህ ላርጋት አይደል እንዴ?!
ነብስ ይማር
ነፍስ ይማር
RIP
ነብስ ይማር ለቤተሰብ መፅናናትን ይስጣችሁ
እደት ለኛ መራት አይቀጥቀጥ
ነብስ ይማር!!!!