#FastMereja I አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ሲሰራበት የቆየዉን የቴክኖሎጂ ዉጤት ከ500 በላይ አበልፃጊዎችን በማሳተፍ ዘርፉን ለማበርታታት ፕሮጀክት ቀርፆ መንቀሳቀስ መጀመሩን በዛሬዉ ዕለት ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘዉ ዋና መስሪያቤቱ ሪያሊቲ ሀንፃ 9ኛ ፎቅ በተሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቋል።
የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳንኤል በቀለ ይሀንን የፈጠራ ዉድድር በዘጠና ቀን ዘመቻ ወደስራ ስናስገባ የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን የቴክኖሎጂ እድገት ካለበት ደረጃ በአጭር ጊዜ የከፍታ ማማላይ ለማድረስ አልመን ነዉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በመርሀ ግብሩም በቅድሚያ የተወዳዳሪዎች ምዝገባ የሚካሄድ ሲሆን ምዝገባዉም እስከ ኖቬምበር 8 ድረስ የሚቆይ ሲሆን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ተማሪዎችን እንዲሁም በዘርፉ በግላቸው የሚንቀሳቀሱ ከ500 በላይ ዌብሳይት አበልፃጊዎችን አወዳድሮ እንደሚሸልም እና ለወጣቶች የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን ይዞ መምጣቱን ገልፀዉ፤ ዉድድሩ በአምስት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚካሄድ እንደሆነና የዌብ ዲዛይነሮች ይህ እድል ሳያመልጣቸዉ እንዲመዘገቡ ጥሪ ያቀረቡት ሀላፊዉ፤ አቅማችሁን በማዉጣት የተሻለ ነገር በመሥራት ብሎም በፍሪላንሰርነት በጋራ እንሥራ የሚል ጥሪ በማቅረብ ለበርካቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር እንቅስቃሴ መሆኑን በጋዜጣዊ መግላጫ መረሀ ግብሩ ወቅት ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የዌብ ዲዛይኑ ትኩረት አድርጎ የሚሰራባቸው የስራ ዘርፎች ኢኮሜርስ፣ ቱሪዝም፣ ሆስፒታሊቲ፣ የሄልዝ ኬር፣ የተማሪዎች ሰርቪስ፣ የማህበረሰባዊ ትስስር ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ማወቅ ተችሏል።





2 comments
አልገባንም
100 ሺ ወይስ 100 ሚሊዮን? 100 ሺ ምን ሊሠሩበት? የገንዘብ አቅሙ እንደሞተ አልሰሙም?