banner

የንግድ ሥርዓቱን ጤናማ እና የተሳለጠ ለማድርግ እየተሠራ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የሀዋሳ ከተማ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ “የገበያ ማዕከላትን በማስፋፋት እና በተዋንያን መካከል መልካም ትስስር በመፍጠር የተሳለጠ ግብይት ለመፍጠር እየተሰራ ነው።

የሀዋሳ ከተማ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ችሎት የንግድ እና ገበያ ልማትን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ልምድ ደካማ እንደነበር ጠቅሰዋል። ይህም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የግብይት ሥርዓቱ ላይ ከፍተት ፈጥሮ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

የከተማው ንግድ እና ገበያ ውጤታማ እንዲሆን ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አብረው የሚጓዙ አዳዲስ አሠራሮች ላይ ግንዛቤ መፍጠር ፣ በረጅሙ የግብይት ሰንሰለት ውስጥ ደላላው ስለሚበዛ ሳይንሳዊ የሆነ የግብይት ትስስር በመፍጠር እና የገበያ መረጃ ሥርዓት መዘርጋት በትኩረት የሚሠራባቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

የግብይት ሥርዓቱን ጤናማ ለማድረግም አዳዲስ ቴክኖሎጀዎችን ለመጠቀም በሂደት ላይ መሆናቸውን አቶ ተመስገን አንስተዋል፡፡

የነዳጅ ምርቶችን ፍጆታዎች እንደ ሃገር ፈተና ሆነውብን ቆይተዋል። ነገር ግን ያለው ችግር በክፍፍል መፍትሄ ለመስጠት ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ በየመሰረቱ ለአሽከርካሪዎች እንዲደርስ እየሰራን እንገኛለን ሲሉም ገልፀልዋል።

በተጨማሪም በሁሉም የንግዱ ዘርፍ ላይ የሚታይ ማንኛውንም አይነት ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴን በተለይ በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ እና በነዳጅ ግብዕይቱ ላይ የሚኖር ህገወጥ ተግባር ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደተቋም እንደሚወሰድ እና እየተወሰደ እንደሆነም አቶ ተመስገን ችሎት አክለዋል።

ለውስን ስግብግብ ነጋዴዎች ሲባል የመላው ህዝባችን በአላስፈላጊ ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት እንዳይጋለጥ እንደ መንግሥት ቁርጠኛ አቋም ይዘናል ብለዋል።

2 comments

ፍቅር ያሸንፋል October 28, 2024 - 5:07 pm

ዜና እንጂ ተግባር ወፍ

Reply
Keka Gezahegn October 28, 2024 - 5:10 pm

በግድ ነው እንዴ ፎቶውን ያነሱት 🤧

Reply

Leave a Comment