0
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የዐረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊ የኾኑትን ሰዒዳ (Saida) ሙሐመድ ዑመር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ አባል በምትኾንበት መንገድ ጉዳይ ዙርያ ሐሳብ ተነስቷል።
የዐረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊዋ ጥያቄው ተገቢውን መስፈርት አሟልቶ በኢትዮጵያ መንግሥት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ከቀረበ ሁኔታዎችን በቅርበት ለመከታተል ያስችላል ብለዋል።
በውይይቱ ላይ የዐረብ ሊግ የፕሬስ ክፍል ኃላፊ ኢብራሂም አል ሱዳኒ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እና የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊው ረዳት ፕሮፈሰር አደም ካሚል ተገኝተዋል።

10 comments
አረብ ምንጊዜም የሀበሻና የኢትዮጵያ ጠላት ነው! አረብ ሊግ መግባት በጣም ብዙ ዋጋ ያስከፍለናል ቢታሰብበት መልካም ነው
𝕕𝕖𝕤 𝕤𝕚𝕝😊
ብር ይስጡን
የብዙ ሀይማኖት መገኛ የሆነችን ሀገር በአንድ ሀይማኖት በተሰባሰበ የአረብ ሊግ ስር ማስገባት ወንጀል ነው።
በሳቅም ሊገሉን እየሞከሩ ነው🤣🤣🤣
በሸሪኢ ኢትዮጽያ ትመራ ነው??? አያዛልቅም ፣አይሆንምም ። ምስጢሩ በቁጥር ከክርስቲያኑ እንበልጣለን ስለዚህ ቁጥራችን ከበዛ ኢትዮጵያ በሸሪአ ትመራለች ነው ጉዳዩ ይህ የአክራሪው/ ውሃብዩ ክንፍ የቆየ የተሳሳተ ህልም ነው። እያዋዙ መጠቅለልን ለማያዝ የተሸረበች ሴራ ናት???
ለጊዜው ከሊጉ ታችኛው ዲቪዚዮን አይሻልም ትላላችሁ?
አዳሜ ስትንጫ ለማየት I can’t wait it
አረብ ሊግ ማለት ምን ማለት ነው??ማንም ሀገር አረብ ሊግ መሆን ይችላል ማለት ነው?? ምንድን ነው እየሆነ ያለው??
የቀን ቅዠት