ኢትዮጺያዊያን እባካችሁ ወደቀልባችን እንመለስ። ሰውን ያህል ፍጡር በመግደል ካደገበት ከኖረበት ማፈናቀል መፈሳዊም ሞራላዊም ትርፍ የለውም ከዛ ይልቅት በብዙ ፈተና ውስጥ ችግር ውስጥ ያለውንመመልከት መርዳት የምንመኘውን የእሱን ርስት ልናገኝ እችላለን።
ቀሲስ ታጋይ ታደለ
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ፀሐፊ
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኀበር ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ በመቄዶንያን አረጋዊያን በተገኙበት የጸሎት መርሀ ግብር ተከናወነ ።
የጸሎት ፕሮግራሙ ዓላማ አረጋዊያንን ጋር ተኩኖ ቢጸለይ ፈጣሪ ሰላሙን፣ ፍቅሩን እንደሚሰጥ በማሰብ
እደሆነ ይህ መርሀግብሩ መዘጋጀቱን
ቀሲስ ታጋይ ታደለ
ለመገናኛ ብዙሀኑና ለተሳታፊው
ገልፀዋል።
ሁሉም የእምነት ተከታዮች በመቄዶንያ አሉ። መቄዶንያ ውስጥ ፕሮቴስታንቶች፣ ሙስሊሞች፣ ኦሮቶዶክሶች፣ ካቶሊኮች አሉ።
ጸሎቱን የሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት አባቶች ሁሉም በዬእምነታቸው መርሀ ግብሩን በጸሎት አስጀምረው፣ የጸሎት መርሀ ግብሩ ተከናውኗል።
የመቄዶንያ መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ
ሁሉም የእምነት ተከታዮች በመቄዶንያ አሉ። መቄዶንያ ውስጥ ፕሮቴስታንቶች፣ ሙስሊሞች፣ ኦሮቶዶክሶች፣ ካቶሊኮች
መቆዶኒያን ምግብ፣ ልብስ መጠለያ ብቻ አይደለም ለነፍሳቸው መንፈሳዊ ፍላጎቶችንም ጭምር ተሟልቶላቸው እዚ እስካሉ ድረስ ወደኋላ የማይለው ነው።
መቆዶኒያ ትንሽዬዋ ኢትዮጲያናት ኑ እውነቱን እዚ አግኙት
በአሁኑ ወቅት በጣም በርካታ ሰዎች እየረዳን እንገኛለን።
5 ወለል ያለው ህንጻ እየገነባን እንገኛለን። በክልሎችም እንደዚሁ በተለያዩ ቦታዎች ግንባታዎች እየተፋጠኑ ይገኛሉ።
ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ ኮንሶ፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ጅማ፣ አምቦ፣ ዓዲግራት፣ ዓድዋና ሌሎችም ቦታዎች መቄዶንያ አለ። በተለይ ደግሞ እኛ የምንረዳቸው የአልጋ ቁራኛ፣ የጎዳና ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን ነው።
ወደመቆዶንያየ85 ዓመት እናቶች ተደፍረው እዚህ የመጡበት አጋጣሚዎች የማንረሳው ክፉ ገጠመን ነውጎዳና ሰዎች በብርድ ምክንያት ይሞታሉ። ብርድ የመታቸው ሰዎች ወደ ህክምና የሚወስዳቸው በማጣታቸው ነው ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ የተገኙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፣ መርሀ ግብሩ የተዘጋጀው ከአረጋዊያኑ ጋር ቢጸለይ ፈጣሪ ጸሎት ይሰማን ተብሎ ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።
“ ዛሬ በመቄዶንያ የተገኘነው ሁለት ጉዳዮችን መሠረት አድርገን ነው። አንደኛው ጸሎት ለማድረግ ነው።
በአገር ሰላም ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የድርሻቸውን እንዲወጡ በማሰብ ጸሎት ማድረግና የሰላም ጥሪ የቀረበላቸው ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመለሱ አስቸኳይ ሁኔታ ለመፍጠር የተደረገ ነው።
ሁለተኛው በመቄዶንያ የተገኘንበት ምክንያት በመቄዶንያ ከ8,000 የሚልቁ ለችግር የተጋለጡ፣ ጎዳና ላይ የወደቁ ኢትዮጵያዊያን ምዕመናን፣ ሙስሊሞች ክርስቲያኖች በኀብረት አሉ።
ስለዚህ ከእነርሱ ጋር ሆነን ብንጸልይ፣ ወደ ፈጣሪ ብናነባ ፈጣሪ ምህረት፣ ቸርነት ያደርግልናል በሚል እሳቤና መቄዶንያም መደገፍ ስላለበት ድጋፍ እንዲደረግለት በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ለማቅረብ ነው።
ስለዚህ ኢትዮጵያዊያን እባካችሁ ወደ ቀልባችን እንመለስ። ሰውን በመግደል፣ በማፈናቀል የምናገኘው ጥቅም የለም። ሰውን በመርዳት ግን ጥቅም ይገኛል። ሰላምን በማረጋገጥ ግን ጥቅም ይገኛል ” ብለዋል።





3 comments
Belew erasachewin chilachew stelyu tewin
በኢትዮጵያ ውስጥ የሀይማኖት ተቋማት እንጁ እምነት እንደሌለ አንድ ጥናት በሀገራችን በሚደርሰው ስቃይ ላይ በመንተራስ እምት እንደሌላቸው ጠቁመዋል።
እኛን እያረጌሙ አሳዲጎን እርደታን ዳግም እኛኑን ይሌምናለ ፍጥረት ሆይ ቴመስጌን እጆቻቺን ሲላስ ጌባቾ ኢኛስ እንዴነንቴ አይዴሌኒም።