0
…
ሰላም በጣም ጥሩና አስፈላጊ ነው። ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላማዊ መንገድ መምጣትም በጣም ደስ የሚል እና የሚበረታታ ተግባር ነው ። አገሩ በጦርነት ተዳክሟል። ህዝቡ ታክቶታል ።
.
ወደሰላም መንገድ የገቡ ታጣቂዎች የሚስተናገዱበት መንገድ ግን በደንብ ሊታሰብበትና ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል።
መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች መሃል ከተማ ከነትጥቃቸው እንዲገቡ ማድረግ ዛሬ የተፈጠረውን አይነት ችግር ይፈጥራል።
.
በመሰረቱ እነዚህን ታጣቂዎች የፈጠራቸውና ወደ ትጥቅ ትግል ያስገባቸው ብዙ ምክንያት ቢኖርም ከዚህ ቀደም ከአስመራ ስምምነት በኋላ የትጥቅ መፍታት እና ወደማህበረሰቡ የመቀላቀል ሂደቱ በአግባቡ አለመካሄዱም ነው ።
.
መንግስት ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ እና አገሩና ህዝቡ እፎይታ እንዲያገኝ ጥረት ማድረጉ ትልቅ ነገር መሆኑ እንዳለ ሆኖ ታጣቂዎች ከስምምነት በኋላ የሚኖራቸው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ግን ሊታሰብበት ይገባል ።
.
ታጣቂዎች ወደ ሰላም ስለመጡ የከተማው ነዋሪ ሰላም ማጣት የለበትም ።
ጋዜጠኛ ኤርሚያስ በጋሻው

10 comments
ሰላም ሆነውም ይበጠብጡናል??😑
እኮ እንድህ ንገርልን
በትክክል። ቼልሲ የለንደን ኩራት ዛሬም አኮራን💙💪💪💪💪
ታስራ የነበረች ጥጃ ስትለቀቅ ልማዷ ነው ያባታችንን ቤት አትረብሹ
እየመጡ ነው እከከ ዘራፍ ወንዱ እያልክ ከርመህ ጥይት ተተኮሰ ብለህ ታላዝናለህ የፍራቻ ጥግ ይሉሃል ይሄነው እንግዲህ
London Is Blue 💙💙💙💙💙😛
የከተማው ነዋሪ ሰላም ማጣት የለበትም የገጠሩ ነዋሪ ግን በደንብ መበጥበጥ አለበት ማለት ነው ? ለዚ አመለካከታቹ እኮ ነው ከገጠር መጥቶ ኑሮአቹን የሚያጦዝባቹ ይበለቹ
ስንት ዓመት ሠላም አጥተህ የለ …ለአንድ ቀን ምነው ከበደክ?
እንዲ እያላቹ ነው ሰላማችንን ያጣነው 😏
ሰላም ምን እንደሆነ ስላሳዩን እናመሰግናለን