0
ቲክቶከር ሮማን በመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 በተባባሪ አዘጋጆች ከሚቀርቡ ዝግጅቶች መካከል አንዱ በሆነው የብርሐን መንገድ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ መቅረቧ ይታውቃል፡፡
የቀረበችው “ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ማዋል” በሚል ከዚህ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ያስተላለፈችውን የተዛቡ አመለካከቶችን በተመለከተ ይቅርታ ለመጠየቅ እና ከስህተቷ ሌሎች ትምህርት እንዲወስዱ ነው፡፡
በመሆኑም በርካታ አድማጮቻችን በግለሰቧ መቅረብ መከፋታቸውን ነግረውናል፡፡ ለተፈጠረው ጉዳይ ጣቢያችን ይቅርታ እየጠየቀ ላልተወሰነ ጊዜ በተባበሪ አዘጋጆች የሚቀረበው የብርሐን መንገድ የተሰኘ ፕሮግራም የታገደ መሆኑን እናሳወቃለን፡፡
በተጨማሪም በቀጥታ ስርጭት ወቅት የፕሮግራሙ አዘጋጆች በቀጥታ ስልክ መስመር የገባ አድማጭን ያቋረጡበት መንገድ ከሙያ ስነምግባር ያፈነገጠ በመሆኑ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
10 comments
የብርሃን መንገድ ደስ ይላል 😂😂😂
Hulemenaye Legesse G
የት አባቱ ዋጋውን ሰጡት ይሄ የማይረባ
ይች አሮጊት 😂😂😂😂
የማንም መሀይም መጫወቻ ሆነ እኮ
Kuku Habte
እስኪ ምን አይነት ስህተት ሰርቼ ራዲዮ ላይ ቀርቤ ይቅርታ ልጠይቅ ሀሳብ አስተያየት ስጡኝ🙄😁
አቅራቢውን ራሱ እኮ ሰሎሞን ሹምዬ ን በዩቲዩብ እቅርቦት ሰለሞን ሹምዬ አየር ላይ አጥቦ አስጥቶት ከእውቀት የፀዳ መሆኑን አጋልጦታል። አሁን ይህቺን ይትልቅ ቀላል ማቅረቡ ምን ይባላል?
ሞጣ ቀርቦ ለምን ሙድ አይዝብንም
መናኸሪያ ነው ማፈሪያ …
Radio ጣቢያው መዘጋትም ነበረበት በምን መስፈርት አቀረባት?