0
(African Book of Records) የምስከር ወረቀት የተሰጠው በአፍሪካ ጃዝ መንደር በተዘጋጀ ዝግጅት ነው፡፡ ድምፃዊ ተስፋዬ ታዬ በሀገራችን ከሚገኙ ከ45 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች የሙዚቃ ስራዎችን ለአድማጮች አቅርቧል፡፡ በነዚህ ስራዎቹም የሀገራችንን ህዝቦች ባህል፣ ቋንቋ አጠቃላይ ማንነት ማስተዋወቅ ችሎዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የአፍሪካ የድንቃድንቆች መዝገብ የክብር የምስከር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡
ተስፋዬ ታዬ ሙዚቃን የጀመረው በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ሲሆን ትምህርቱንም እዳጠናቀቀ ወደ ራስ ቲያትር በመግባት ለ አምስት አመታት ካገለገለ በኃላ የሚያስባቸውን ስራ ለመሰራት ስራውን በመልቀቅ በተለያዮ አካባቢዎች በመዞር ስራውን በግሉ መስራት ጀመረ የአልበም ስራም በመስራት 2 አልበሞችን ለአድማጭ አብቅቷል በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በመዞር በርካታ ስራዎችን ሰርቷል አሁንም በመሰራት ላይ ይገኛል በስራ ሂወቱም ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል እያገለገለም ይገኛል።





3 comments
ይገባዋል
ይገባዋል🙏🙏🙏🙏
ሸላሚ ወይስ መዝጋቢ ?
ተሸለመ ወይስ ተመዘገበ ?
ተስፋዬ ጥረቱ ውጤቱ ለአስተማሪነቱ ከሽልማት በላይ ይገባዋል!
ጉዳዩ ግን ጥያቄ ያጭራል
አፍሪካ ድንቃድንቅ እንደስሙ ድንቃድንቅ ጉዳዮችን መመዝገብ እና ለተመዝጋቢው ማረጋገጫ መስጠት ነው ተግባሩ ወይንስ ሸላሚ ?
ተስፋዬስ በተገለፀው እና ባልተገለፁት ውጤታማ የሙዚቃ ተግባራቱ ከባህልና ቱሪዝም እና በዘርፉ ከሚሰራ ተቋም እንጂ እንዲህ ባለ ሁነት መሸለም ይበልጣል ወይ ?
ሸላሚ ላይ ግን የዘርፉ ቁንጮን ጋብዞ ማሸለሙ ግን የሚያስመሰግን ነው