banner

አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል የመልህቅ አምባሳደር ሆነች

#FastMereja I አራተኛው መልህቅ የስነ ፅሁፍ ምሽት በአዲስ አበባ ካፍደም ሲኒማ ተከናወነ። አርቲስቶች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ ኮሜዲያኖችና የሃገራችን ታዋቂ ባለሙያዎች በተገኙበት መርሃ ግብሩ ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓም ተካሂዷል። በአዳዲስ እና ታዋቂ ገጣሚያን ግጥም ቀርቧል፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ኮሜዲ፣ ዳንስ፣ የአንድ ሰው ተውኔት በመድረኩ ላይ ለታዳሚያን ቀርቧል።

በእለቱ ዝነኛዋ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል የመልህቅ ኪን የክብር አምባሳደር በመሆን የመልህቅ ዝግጅት እንድታስተዋውቅ የክብር ካባ በመድረኩ ላይ ተሸልማለች።

አዘጋጁ መልህቅ ኪን ፕሮዳክሽን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ኪነጥበባዊ ፋይዳ ለመስጠት የተቋቋመ እንደሆነ ተገልጿል። በተለይ በኪነጥበቡ መስክ ለሀገራችን እና ለወገኖቻችን ታላቅ ስራ የሰሩ ባለሙያዎች በህይወት የሌሉትን በመዘከር ለቤተሰቦቻቸው የምስጋና ሰርተፊኬት እና የካባ ማልበስ እንዲሁም በህይወት ያሉትን ደግሞ በመድረክ ላይ ክብር የመስጠት እና የመሸለም ስራዎችን ሲሰራ እንደቆየ ተነግሯል።





Leave a Comment