0
በመዲናችን የሚካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ተከልክሏል።
ስለሆነም ከዛሬ የካቲት 04/2017 ዓ.ም ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 09/2017 ዓ.ም ድረስ በመዲናዋ በየትኛውም አካባቢ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የማይቻል መሆኑን ቢሮው ከወዲሁ ያሳውቃል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ