0
#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ኢስት አፍሪካ ድርጅት የህንፃ ግንባታ ድርጅት በኮሪደር ልማት በተሠራ አስፓልት በማቆሸሹ በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦፊሠሮች 300,000 /ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣቱ ገለፀ።
ድርጅቱ በተደጋጋሚ ግንዛቤ ተፈጥሮለት ከዚህ በፊት 100 ሺህ ብር የተቀጣ ሲሆን ድጋሚ ተመመሳሳይ ጥፋት በመፈጸሙ የቅጣቱ እጥፍ 200 ሺህ ብር በድምሩ 300,000 /ሦስት መቶ ሺህ/ ብር ተቀጥቷል ።
መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
#ልዩ_ልዩ

10 comments
የታለ
Minewu mengedu alga hone inde akoshe malet
እርምጃ መወሰዱ ተገቢ ነው ::
ነገር ግን አንዳንድ ሰወች ልማት አገራች በማማሯ የሚናደዱ የሚተቹ ሰወች ሳይ ይገርመኛል::
ኮሪደር ልማት የገቢ ምንጭ ሁኗል
እና.. ልማታዊ ወንጀለኛ ነዋ!
እንግዲህ እንደ spider man እየዘለሉ አይሰሩ አረ ወ/ሮ አዳነች የካድሬ እውቀቶ ይቅርቦትና ወደ ሳይንሱ ይመለሱ
እኔ የት ሆኖ ያልማ😊
አዳነች አበቤ ይህንን ዜና ስትሰማ ጨርቅዋን ትጥላለች😊
ባህር በር ሆነኮ ነገሩ
ስጀምር ኮሪደሩ የታለህ ኮብልስቶን መንገድ ኮሪደር ብሎ መቅጣት ገንዘብ መውደድ ያሳያል 🤪