#FastMereja I ጓደኛሞቹ የገና ስጦታ ሎተሪን የ1ኛ ዕጣ 10 ሚሊዮን ብሩን ለሁለት ተካፍለውታል፡፡ ጓደኛሞቹ ገደፋው ከበደ እና ሙላቱ መንግስቴ በስራ ቦታቸው አካባቢ ካዛንችስ ብዙውን ጊዜ ቁርስ በሚበሉበት ምግብ ቤት ቁርስ እየበሉ ሎተሪ አዟሪ ወዳሉበት ይመጣል፡፡
ሙላቱ መንግስቴ ለረጅም አመታት የሎተሪ ደንበኛ ሲሆን ገደፋው ሎተሪ አልፎ አልፎ እንደሚቆርጥ ይናገራል፡፡ ሙላቱ በኪሱ ያለው 20 ብር ብቻ በመሆኑ የገና ስጦታ ሎተሪ አንድ ትኬት ብቻ ገዝቶ የተቀሩትን ሁለት ትኬቶች ጓደኛውን ቁረጥ ይለዋል፡፡ ገደፋው እያንገራገረ 40 ብር ከፍሎ ሁለቱን ትኬት ይወስዳል፡፡
የገና ስጦታ ሎተሪ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ሲወጣ ገደፋው ከበደ በሁለቱ ትኬት የ6.66 ሚሊዮን ብር፣ ሙላቱ መንግስቴ በአንድ ትኬት የ3.33 ሚሊዮን ብር እድለኛ ሆነዋል፡፡ ገደፋው ከበደ ህንፃ በሚገነባበት አንድ ጥግ ቦታ በምትገኝ አነስተኛ የሽሮ ቤት የሚተዳደር ሲሆን ሙላቱ መንግስቴ በጎዳና እየተዘዋወረ መጽሐፍ ይሸጣል፡፡
ጓደኛሞቹ የደረሳቸውን ገንዘብ በምን ስራ ላይ እንደሚያውሉት ለጊዜው እንዳላቀዱ፤ሆኖም ተመካክረን የኛንና የቤተሰብን ህይወት የሚለውጥ ስራ እንጀምራለን ማለታቸውን ከብሄራዊ ሎተሪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
#ልዩ_ልዩ

10 comments
ምገርም ጓደኝነት
Endet Des yilal yene wudoch♥️ enkuan tesakalachew
Luck is greater than knowledge
እድል እንዲህ ነዉ
ድሮ ብሩ ዋጋ ነበረው አሁን 3 ሚልዮን ሽሮቤት ማይከፍትበት ዘመን
Woowww
ደስ ስል እግዚአብሔር ይመስገን
Nahom Tsegaye
100k ለማን አስቀሯት? 😂
Fake Lottery nw. Bemetewewek Ye Wetelachu.
Ye Hunat nw Mehelachu National Lottery Rasu Fake nw.