banner

በምሽት የንግድ ቤቶች እና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ለማራዘም በወጣው ደንብ ፀደቀ።

#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው 4ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በሚከተሉት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል::

1. ሀገራዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ ላላቸው የማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች ፕሮጀክቶች የሚውሉ የቦታ ጥያቄዎችን መርምሮ አፅድቋል::

2. መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ ይረዳ ዘንድ የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

3. በምሽት የንግድ ቤቶች እና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ለማራዘም በወጣው ደንብ ዝርዝር ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

4. የተርሚናል አገልግሎት አሠራር እና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

5. የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ አደረጃጀት እና አሠራርን ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

6. የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 166/2016 ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

7. የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ለመተግበር የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል::




1 comment

Mule Getachew March 8, 2025 - 4:23 pm

ከ ትጸልይ በዋላ ነዉ😢😂😂

Reply

Leave a Comment