banner

15ሺ ሰው የሚሳተፍበት የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ተዘጋጀ

#FastMereja I ሜሪጆይ ኢትዮጵያ «አረጋውያንን እመግባለሁ ጤንነቴን እጠብቃለሁ» በማለት መጋቢት 28/2017 ዓ.ም ከ12 ሺህ እስከ 15 ሺህ ሰው የሚሳተፍበት የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ከብራይት አድቨርት እና ኢቨንት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ መነሻውን ኡራኤል መድረሻውን ወሎ ሰፈር ያደረገ የሩጫ ውድድር መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ቲሸርቱ በዳሽን ባንክ እና በቴሌብር የሚሸጥ ሲሆን በተጨማሪም በሜሪጆይ ማዕከላት አስኮ፣ መገናኛ፣ ገዳም ሰፈር ይገኛል፣ ቲሸርቱ የህፃናት በ300 ብር፣ የአዋቂ በ500 ብር ነው እየተሸጠ ይገኛል።

የሩጫ ውድድሩ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በቀጣይ በአርባምንጭ፣ በሐዋሳ እንደሚካሄድ ተነግሯል።

የአሜሪካው USAID ድርጅት ስራ ማቆሙ በርካታ ፕሮጀክቶችን እንድናጥፍ እና ከ100 በላይ ሰራተኞች ስራ እንዲያቆሙ ማድረጉን የሜሪጆይ ኢትዮጵያ መስራች ሲሰተር ዘቢደር ገልጻለች። በተጨማሪም ውሳኔው ቆም ብለን እርስበርስ መረዳዳትን እንድናጎለብት ያደረገን ውሳኔ ነው ብለዋል።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በፊት በ1986 ዓ.ም የተመሰረተ አገር በቀል የግብረ ሰናይና የልማት ድርጅት ነው።





1 comment

Senteryu Adero March 19, 2025 - 9:19 am

ቡና ሰንት ጊዜ ጠየቀ አረ መልሰ ይሰጠን?

Reply

Leave a Comment