#FastMereja I ኮንፍረንስ አስመልክቶ በጦር መሳሪያ አንድን አገልጋይ ማጀብ እንደ ወንጌል አማኝ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው ከአስተምሮት ውጪ መሆኑን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ካውንስል አስታወቀ።
የካውንስሉ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ፓስተር
ጌትነት ለማ በሰጡት መግለጫ የመንግስት አካላት ለአንድ አገልጋይ ፖሊስ አሰልፈው፣ መሳሪያ አስታጥቀው፣ አጀብ ፈጥረው ግርግር በማድረግ የሆነ አካል ወደ ከተማው የገባ የሚያስመስሉት ነገር ተገቢ እንዳልሆነ ተናግሯል።
እንደዚህ አጀብ ስላደረጋችሁ ለወንጌል አማኞች ክብር አይደለም፣ ብዙ አማኞች የመቃብር ስፍራ የላቸውም፣ የማምለኪያ ስፍራ የላቸውም እሱን አድርጉልን ብለዋል።
ጦሩ የመንግስት ነው፣ ሰራዊቱ የመንግስት ነው እጀባ አያስፈልግም ተብሏል። እንደዚህ በሚያደርጉ አገልጋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰደ ካውንስሉ አስጠንቅቋል።
እጀባው ትርጉም አልባ ነው ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው በጦር መሳሪያ መታጀብ ትርጉሙ ሌላ ነው ፍርሃት ሲኖር ነው መታጀቡ የሚመጣው፣ አገልጋዩ ከህዝብ የተበደረው ገንዘብ ሲኖር ችግር የሚፈጥርብኝ ህዝብ ይኖራል ብሎ ሲፈራ ነው በፖሊስ የሚታጀበው እንጂ ወንጌል ለመስበክ ከሆነ እጀባ አያስፈልገውም ብለዋል።
በተደጋጋሚ እንደዚህ የሚያደርጉ አገልጋዮች በፅሁፍ፣ በአካል ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል በቅርቡ እርምጃ ወስደን መግለጫ እንሰጣለን ብለዋል።
በተጨማሪም ዘይት የሚሸጡ አገልጋዮች ከመንግስት ንግድ ፍቃድ አውጥተው ሱቅ ከፍተው ዘይታቸውን መሸጥ ይችላሉ እንጂ በካውንስሉ ፍቃድ ዘይት የሚቸበችቡ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል።

10 comments
ተግባር ወሬሬሬሬ ምንም አይሰራም !!!!!
Sra nwu minchigir alewu
እንዴ ለምን ገቢ አደል 🤨
እዩ ጩፋ የሚባለው ባለስልጣን ሆኖ ይሆን እንዴ ????
መንግሰት ደግሞ እንደ መንግሥት የሲዳማን ክልል ሰላምና የፀጥታ ቢሮ እና የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ መጠየቅ አለበት
ነገርየው ትንሽ አልተገላበጠባችሁም 🤔
በሀይማኖት ስም እጀባውን የሚያካሂደውን ሰው ነው መከልከል
ወይስ ገንዘብ ተቀብሎ የሚያጅበውን ፖሊስ
አንተም ነገ አጅቡኝ ከማለት አትመለስም …. ብሩ ነው የቸገረህ አሁንም !!
ካውንስሉ እራሱ ላቦሩ ነው
Kkkkkkk ስለ ዜይቱ ያወራችውት part ተመችታኛለች
ዘመኑ ዘመነ ሁኗል በኔ ሀገር
ሸገር ላይ ያለኸዉ እዴት ነዉ ያንታገር¿
ስጀመር አግልግሎት ድሮ ቀረ አሁን እኮ ህይወትህን ለመቀዬር የምገባበት አዋጭ የቢዝነስ ዘርፍ ነው ።