#FastMereja I ታላላቅ ሙዚቃ አቀናባሪዎች የተሳተፉበት “ደጃዝማች” የተሰኘው የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ስምንተኛ አልበሟ የፊታችን አርብ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ለህዝብ ጆሮ እንደሚቀርብ በዛሬው ዕለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ለሰባት ዓመታት በደከመችበት “ደጃዝማች ” በተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም ላይ አስራ ሶስት ዘፈኖችን የያዘ ሲሆን ከእነዚህ አስራ ሶስት ዘፈኖች ውስጥ የስምንቱ ዘፈኖች ግጥምና ዜማ የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ሲሆኑ ሌሎቹን ሙዚቃዎች ደግሞ በግጥም ገጣሚ ይልማ ገብረአብ፣ ገጣሚ መሰለ አስማማው፣ ገጣሚ ናትናኤል ግርማቸው የሰሩ ሲሆን ሞገስ ተካ እና ምስክር አወል ግጥምና ዜማ በመስራት በአልበሙ ላይ ተሳትፈዋል ተብሏል።
ከተቀሩት ስራዎች ውስጥ “ወለላዬ” የተሰኘው ሙዚቃ ደግሞ የኩኩ የድሮ ስራ ሲሆን ቴዲ ማክ እንደገና ሪአሬንጅ (Re Arrange) አድርጎ የሰራው መዚቃ ነው የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ “ደዳዝማች” በተሰኘው አዲስ አልበም ላይ ስመጥር የሆኑ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን የሙዚቃ አቀናባሪው አቤል ጳውሎስ ዘጠኙን መዚቃዎች በማቀናበር እንዲሁም አስራ አንዱን ሙዚቃዎች ሚክስ በማድረግ ተሳትፏል።
ሁለቱን ሙዚቃዎች አሬንጅ ያደረገው ማሩ ዓለማየሁ ሲሆን ሙዚቀኛ ያሬድ ተፈራ ፣ ሙዚቀኛ ኡክሊሉ ወ/ዮሀንስ (ጆኒ ሳክስ) እና ሙዚቀኛ ዘሪሁን በለጠ በሳክስፎን ፣ ግሩም መዝሙር እና ሳሙኤል አሰፋ በጊታር ተሳትፈዋል ። “ደጃዝማች”ን ሙሉውን አልበም ማስተር ሳውንድ የሰራው ኪሩቤል ተስፋዬ ነዉ።
ድምጻዊት ኩኩ ሰብስቤ በሐገራችን ውስጥ አሉ ከሚባሉ ገጣሚያን፣ የዜማ ደራሲያን የሚዚቃ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ለሰባት ዓመታት ብዙ ደክማ የሰራችውን “ደጃዝማች” የተሰኘውን ስምንተኛ አልበሟን የፊታችን አርብ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በእራሷ በኩኩ ሰብስቤ የዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያ ለአድማጭ ይደርሳል ተብሏል።
#ኪነ_ጥበብ



3 comments
የዘፈን ጡረታ የለውም እንዴ
ምን ይጠበስ ታዲያ
በጊዜ እንደዘሪቱ እጅሽንና ልብሽን ለጌታ ስጪ ሞተሽ ሲኦል ሳትገቢ