#FastMereja I በኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት ዓስርት ዓመታት የሪል ስቴት ዘርፍ የካበተ ልምድ ያለው ጊፍት ሪል ስቴት “መኖር በጊፍት መንደር” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛውን የሽያጭ ኤክስፖ እስከ ሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም እያካሄደ ይገኛል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣውን የደንበኞችን ፍላጎት እንዲሁም ከጊዜው ጋር ተመራጭ የሆነ ዲዛይንና አዳዲስ እሴቶችን በማካተት ቅንጡ አፓርትመንቶችንና የንግድ ሱቆችን አለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ ኮንትራክተሮች ከልዩ ዲዛይን ጋር የተለያየ መጠን ያላቸው መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ሱቆችን በጥራት እየገነባ ለሽያጭ አቅርቧል።
የጊፍት ሪልስቴት የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብርቁ ይርጋ እንደገለጹት ጊፍት ሪል ስቴት ዓለም የደረሰበትን የግንባታ ቴክኖሎጅን በመጠቀም በጥራት በመገንባት፣ የደንበኞችን ቃል ጠብቀን ቤቶችን ገንብተን በወቅቱ በማስረከብ ግንባር ቀደም ተመራጭ የሆንና ይህንን ተከትሎ በማህበረሰቡ ዘንድ ተወዳጅ ስምና ዝናን አትርፈናል ብሏል።
የጊፍት ሪል ስቴት የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ምክትል ዳይሬክተር ወይዘሪት ሮዛ ዘውዱ የመጀመሪያው ዙር ሽያጭ ከአንድ መቶ በላይ ቤቶች መሸጣቸውን ጠቁመው ሁለተኛው ዙር የዕድሜ ልክ ኢንቨስትመንት ባለቤት ለመሆን ወደ ሽያጭ ቢሮዎቻቸው በመምጣት እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
ጊፍት ሪል ስቴት ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እስከ 30% ታላቅ ቅናሽ በማድረግ፤ ከ9%-25% ቅድመ ክፍያ በሽያጭ ላይ ይገኛሉ። ቀድመው በመምጣት ቤት ፈላጊው የቅናሹ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
ለኑሮ ምቹ በሆነው በዚህ መንደር ትምህርት ቤቶች፣ የህክምና ተቋማት፣ ሞሎች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች ከበቂ የመኪና ማቆሚያ ጋር ተካተዋል።
ጊፍት ሪል ስቴት አዳዲስ ሦስት መንደሮችን ጨርሶ ለቤት ባለቤቶች ካስረከበ በኋላ በአራተኛው የጊፍት ሜትሮፖሊታን መንደር በለገሃር 4 ሺህ ቤቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም በሁለተኛና ሶስተኛ ዙሮች የሚገነቡ 8 ሺህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን እንዲሁም በ6 ኪሎ፣ በቦሌ መድሃኒዓለም፣ በፊጋ፣ በ22 ማዞሪያ፣ በተክለሃይማኖት፣ በሲኤምሲ እና በሌሎች አካባቢዎች 4 ሺህ ቤቶችን በአጠቃላይ ከ16 ሺህ በላይ ቤቶችን ለሽያጭ አቅርቧል።




