banner

ረቂቅ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በኦቲዝም ላይ አስተዋጾ ላደረጉ ግለሰቦች እውቅና ሰጠ።

#FastMereja I ረቂቅ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በኦቲዝም የንግግር ወጌሻ መሰረታዊ ንጽህና ክህሎት ስልጠና፣ የአመጋገብ ክህሎት ስልጠና፣ የአካል ጥንካሬ ስልጠና፤ የትኩረትና ማስተዋል ክህሎት ስልጠናዎች የሚሰጥ ማዕከል ነው።

ማዕከሉ ዛሬ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም በኦቲዝም ግንዛቤ መስጠት ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የእውቅና መርሃ ግብር በመኮንኖች ክበብ አካሄዷል።

የረቂቅ ትምህርትና ስልጠና ኦቲዝም ማዕከል መስራች እና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት ይጨነቁ ባደረጉት ንግግር በአንድ የኦቲዝም ህፃን ልጅ የተነሳ በ2013 የተቋቋመው ማዕከሉ አሁን ላይ 400 የሚያህሉ ህፃናትን በስሩ እንደያዘ ተናግሯል።

ማዕከሉ በመነሃሪያ ሬዲዮ የፕሮግራም አዘጋጅ የሆነችውን እስከዳር አሰፋ የማዕከሉ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ በዛሬው መርሃ ግብር ላይ ሾሟል።

ከዚህ በተጨማሪም በዛሬው እለት በኦቲዝም ግንዛቤ መስጠት ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ እንዲሁም እየሰሩ ለሚገኙ 12 ግለሰቦች የካባ ስጦታ እና የእውቅና አሰጣጥ ተከናውኗል።

ረቂቅ ትምህርትና ስልጠና ኦቲዝም ማዕከል ከተመሰረተ ጀምሮ ከዘጠኝ ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ አገልግሎት ተደራሽ የሆኑ ስራዎችን ማከናወኑ ተገለጸ።





Leave a Comment