0
#FastMereja I ካቮድ ኮሜርሻል የንግድ ሞሎችን እየገነባ የሚገኝ ሲሆን ከሚገነቡ 17 ፕሮጀክቶች አራተኛው “ካዛንቺስ ሞል” ዛሬ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም በካዛንቺስ ሽያጭ ተጀምሯል።
6,762 ካሬ ላይ ያረፈ ግዙፍ የገበያ ማዕከል ሲሆን ከ6 እስከ 9 ወር ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ የሽያጭ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጀማል አብዱልቃድር ገልጿል።
ካዛንቺስ ሞል ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በመሆን የሚገነባ ሲሆን በሚገነባው ሞል ላይም ቀደም ሲል በካዛንቺስ በንግድ ላይ ተሰማርተው ይሰሩ የነበሩ ግለሰቦች ቅድሚያ ተሰጥቶ በቅናሽ ወደ ሞሉ እንዲገቡ እንደሚደረግ ተነግሯል።
በአሁኑ ወቅትም ተደራጅተው የጠየቁ 200 ሰዎች እንደምርጫቸው ምዝገባው እንደተከናወነ ተገልጿል።
ካዛንቺስ ሞል በውስጡ ደረጃውን የጠበቀ ሲኒማ፣ ሬስቶራንቶች፣ ዘመናዊ የልብስ አዳራሾች፣ ስፓ እና የውበት መጠበቂያዎች እንዲሁም የመጨረሻው ወለል ላይ በአይነቱ ለየት ያለ ወተር ፓርክ ይኖረዋል።




