0
#FastMereja I በ2017 ዓ.ም. በየትምህርት ቤቱ እና ስልጠና ማዕከሎች የኮዲንግ፣ ሮቦቲክስ እና ኢንጂነሪንግ ስልጠና የወሰዱ ልጆች የዓመቱ መዝጊያ የስቲም ፌር (STEM fair) ዛሬ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ተካሄደ።
የስቲም ፌር መርሃ ግብሩ ዓላማ ልጆች ሳይንሳዊ ፕሮጀክቶቻቸውን እንዲያሳዩ፣ እርስ በርስ የመማር ተሞክሮዎች እንዲካፈሉና ለሳይንስ ያላቸውን ፍላጎትና ችሎታ እንዲያሳዩ መድረክ ማመቻቸት እንደሆነ STEM for Kids በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ኃ/ማርያም ገልጿል።
በመርሃ ግብሩ ላይም ከ60 በላይ የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ያዳበሯቸውን ክህሎቶች ያሳዩ ሲሆን፤ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችም ሽልማት ተቀብሏል።
ሶ ኢዝ ቴክኖሎጂ እና ስልጠና ኃ/የተ/የግ/ማ (STEM For Kids) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፍሬንቻይዝ ድርጅት ሲሆን፤ ባለፉት 2 ዓመት ከ8 ወራት እድሜያቸው ከ4 እስክ 17 ለሆኑ 4ሺህ ታዳጊ ልጆች የቴክኖሎጂ ክህሎቶች ትምህርቶችን ሲሰጥ ቆይቷል።




