#FastMereja I በ2018 ምርት ዘመን 100 ቶን የታጠበ ቡና ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ ማቀዱን ወርቁ ቡቼ የቃዴላ ቡና አቅራቢና ላኪ ድርጅት ገለፀ። ድርጅቱ ይህንን የገለፀው 10ኛ ዓመት የሰራተኞች ማነቃቂያ ክብረ በዓል ባከበረበት ወቅት ነበር።
በ1966 ዓ.ም በሲዳማ ክልል በቡርሳ ወረዳ ጫንጮና ሽጋዶ ቀበሌ፤ የዛሬው የቃዴላ ቡና አቅራቢና ላኪ የግል ድርጅት ባለቤት አቶ ወርቁ ቡቼ የተወለደበት መንደር ነዉ፡፡ እንደ አርሶ አደር ቤተሰብ ልጅ መሰረታዊ የቀለም ትምህርቱን በአከባቢዉ በሚገኝ የገጠር ትምህርት ቤት የጀመረ ቢሆንም ብዙም ሳይገፋበት በ1989 ዓ.ም በ120 ብር መነሻ ካፒታል በመንደሩ ወደ ጥቃቅን ንግድ ዘርፉን ማለማመድ እንደጀመሩ የህይውት ታሪካቸው ያስረዳል ፡፡
በኋላም አባታቸው ለሥራና ኑሮ የተሻለ አከባቢ ፍለጋ ወደ አሮሬሳ ወረዳ ተንቀሳቅሶ በኖሩበት አቶ ወርቁም በመጆ ከተማ መኖሪያ አድርጎ፤ በወቅቱ አከባቢ ቅቤ እርካሽ ስለነበር ከአሮሬሳ የተለያዩ ገጠር ገበያዎችን በእግር እየዞረ ቅቤ እየገዛ በማጠራቀም ወደ ቅርብ ከተሞች በማቅረብ እየሸጠ የሚገኘውን ትርፍ ምንም ሳያባክን በመቆጠብ ማጠራቀም እንደጀመረና የገንዘብ ካፒታሉንም ቀስ በቀስ እስከ 100,000 ብር ካደረሰ በኋላ ከአከባቢ ገበያ አልፎ እሰከ አለታ ወንዶና ዲላ ከተማ ድረስ በማከፋፈል የንግድ ሥራውን ማስፋፋት ቀጠለ።
ከቅቤ ንግድ በተጨማሪ የእህል ንግድ ጀምሮ፤ ቅቤና የእህልን ንግድን ባንድ ላይ በማጣመር ሁለቱንም የንግድ ዘርፍ ውጤታማ አድርጎ ማስቀጠሉንም በክብረ በዓሉ መድረክ ላይ ተናግሯል ።
በመቀጠልም አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ የንግድ መነሻ ዋና አንቀሳቃሽ በሆነዉ እቁብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረዳጃ ቡድን ውስጥ በመግባት ዕጣ መጣል የጀመረው አቶ ወርቁ ለመጀመሪያ ከዕቁብ በተገኘ ገንዘብና በሁለቱም ንግዶች ባጠራቀመው ገንዘብ ለንግድ ስራ ለማቀለጠፍ እንዲረዳዉ ለመጀመሪያ ጊዜ በ250,000 ብር አይሱዙ የጭነት መኪና በመግዛት የገብስና ስንዴ ጅምላ ንግዱን በሙሉ አቅሙ መቀላቀሉንም አውስቷል ፡፡
ቀጥሎም አከባቢው ከፍተኛ የታጠበ ቡና የሚዘጋጅበት አከባቢ በመሆኑ ከአርሶ አደር አከባቢ ቀይ እሸት ቡና በመሰብሰብ ለታጠበ ቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪዎች ማቅረብም ፤በገዛዉ አይሱዙ መኪና በመጠቀም ከቡና ማቅረብ በተጨማሪ በአከባቢዉ በብዛት የሚመረተውን ስንዴና ገብስ በመሰብሰብ ወደ ትልልቅ ከተሞች ማከፋፈሉን መጀመራቸውንም አንስቷል ፡፡
የካፒታል መጠንና የንግድ ዘርፍንም እያስፋፉ በፍጥነት በማሳደግ በጸሐይ ኃይል የሚደርቅ ልዩ ቡና ስፔሻሊቲ Sun dried spcecilaity coffee ፈቃድ በማውጣት በግል ህጋዊ ፊቃድ የቡና ዝግጅት በ2002 ዓ.ም በመጀመር ዘርፉን ሙሉ በሙሉ በመቀላቀል፤ በጅምር አከባቢ ብዙ ውጣ ውረድ ያለበት ቢሆንም የቡና ሥራ አዋጭ መሆኑን በመገንዘብ ይህንን ዘርፍ ከምን ጊዜም በላይ አጠናክሮ የቀጠለዉ እና በቡና ሥራ ተነቃቅተው ፤ የቀደምት የቡና አቅራቢዎችን ፈለግ በመከተል፤ በ2006 ዓ.ም የራቻ ባሌሳ የእሼት ቡና አክሲዮን ማህበር እንዱስትሪ በመቀላቀል ደረቅ ብቻ ሳይሆን የታጠበ ቡና ማዘጋጀት ጀምረዉ ዛሬ ስድስት የእሼት ቡና መፈልፈያ እንዱስትሪ በሲዳማ ክልል እና ሁለት የእሼት ቡና መፈልፈያ እንዱስትሪ በደቡብ ክልል በጌደኦ ዞን በድምሩ የስምንት የእሼት ቡና መፈልፈያ እንዱስትሪ እና አንድ ደረቅ ልዩ ቡና መፈልፈያ ባለቤት መሆን መቻላቸውንም ተናግሯል ፡፡
በተጨማሪም በ2014 ዓ.ም ቡናን ወደ ውጪ ላኪነት ፈቃድ በማግኘት የታጠበና ስፔሻሊት ቡና በብዛት ወደ ውጪ አገር መላክ ጀምረዉ በአሁኑ ጊዜ ከ60 ቶን በላይ ቡና ምርት ለዉጪ ገበያ ማቅረብ እንደቻለ አቶ ወርቁ ቡቼ አሥረኛ ዓመት የምሥጋና የሰራተኞች ማነቃቂያ ክብረ በዓል መድረክ ላይ ተናግሯል ።
ድርጅታቸው በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ድርጅቶች ሥር ከ1ሺ 6 መቶ በላይ ጊዜያዊ እና ከ300 በለይ ቋሚ ሠራተኞች በድምሩ 1ሺ 9 መቶ በላይ ዜጎች የሥራ እድል የፈጠረ መሆኑንም ገልጿል ።
የሀገር ልማት ዋና ምንጭ የሆነውን ገቢ ግብርን በተመለከተ ከአሮሬሳ ወረዳ ጀምሮ እስከ ፌደራል ድረስ ግብርን በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል ድርጅቱ ተሸላሚ መሆኑንም አንስቷል አቶ ወርቁ በንግግራቸው ።
በ2018 የምርት ዓመትም የኢትዮጵያ ቡና ተፈላጊነትና ዋጋ ሳይቀንስ ይቀጥላል የሚለዉን ግምት ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ሁሉም የቡና ሳይቶች ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ማድረግና ለሥራ ልዩ ትኩረት በመስጠት እሰከ 100 ቶን የቡና ምርት ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ በሚያስችል መልኩ ከወዲሁ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውንም አመልክቷል ።
በመቀጠልም የቡና ምርታማነትን- በፐርሰንት፤
የቡና ጥራትን- በደረጃ ፤የፋይናንስ አጠቃቀም እና ዉጤታማነትን፤የቡድን ሥራ ዉጤታማነትን እና ወዘተ መሠረት በማድረግ ዉጤታማ የሆነ ሳይት እና ሠራተኞች በዉጤቱ የሚገኘዉን ትርፍ በድርጅቱ ደንብ መሠረት እንዲከፋፈሉ ማቀዱንም አብስሯል ።
በዕለቱም ባለፈው ሥራ ዓመት ላሳዩት አርአያነት ላለው ተግባር፤ እንደየስራ እንቅስቃሴያቸውና ካስመዘገቡት ውጤት አንጻር ለኃላፊዎችና ለባለሙያዎች ለማነቀቂያ የሚሆን ሠርቲፊኬትና የገንዘብ ሽልማት በመስጠት በዓሉ ተጠናቋል ።




