0
#FastMereja I የሐጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ አዘጋጅ የሆነው ሐጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳን ከሸለመ በኋላ በህዝቡ ቅሬታ አጋጥሞታል። በተለይ የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ህይወቷ ከማለፉ በፊት ጥቃት ይደርስባት እንደነበር የሚያመለክቱ ምስሎች ከወጡ በኋላ በህዝቡ ዘንድ ቁጭት እና እልህ የታከለበት እንደ አዲስ ጉዳዩ እንዲነሳ ሆኗል።
ይህንንም ተከትሎ የሞዴል ቀነኒ አዱኛ እጮኛ የነበረው ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ የተሸለመው ሽልማት ተነጥቆ ፋውንዴሽኑ በ24 ሰዓት ውስጥ ለህዝቡ መግለጫ እንዲሰጥ ዘመቻም ተጀምሮ 24 ሰዓት ቢሞላውም ከፋውንዴሽኑ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ ባለመኖሩ ፋውንዴሽኑ በውሳኔው ጸንቷል።
