banner

30 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ርክክብ ተደረገ

#FastMereja I ሄኖሲስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ዛሬ ሐምሌ 02/2017 ዓ.ም በተከናወነ ስነ ስርዓት ከኢትዮ ኢቪ ሞተርስ ጋር በመተባበር 30 የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ለአራራይ የታክሲ ዘርፍ ማህበር አስረክበዋል።

ሄኖሲስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር በቀጣይ ዙር ለ700 የአራራይ የታክሲ ዘርፍ ማህበር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ማስረከቡን እንደሚቀጥል ተነግሯል።

ተሽከርካሪ የተረከቡ የአራራይ ታክሲ ዘርፍ ማህበር አባላት ከዚህ ቀደም ከሌላ ድርጅት ጋር ገንዘብ ከፍለን ተሽከርካሪዎችን ብንጠባበቅም የውሃ ሽታ ሆኖ ድርጅቱ ገንዘባችንን ወስዶ ተሽከርካሪውንም ሳናገኝ ቀርተናል አሁን ከሄኖሲስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር በአጭር ቀናት ውስጥ ቆጥበን ተሽከርካሪ ተረክበናል ሌሎች የማህበሩ አባላትም የእድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።

ሄኖሲስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም. 50 አባላትን ይዞ የተመሰረተ ህብረት ስራ ማህበር ሲሆን በአሁን ሰዓት ከ150 በላይ አባላት አሉት፡፡





1 comment

Tesfaye Ybebal Akalu July 9, 2025 - 4:13 pm

የደንነታቸዉ ጉዳይ ተርስቷል

Reply

Leave a Comment