banner

የድምጻዊ ሔኖክ ጥጋቡ የሙዚቃ አልበም ለህዝብ ሊደርስ ነው።

#FastMereja I በፋና ላምሮት ውድድር ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኘው ድምጻዊ ሔኖክ ጥጋቡ “ዉብ ዓለም” የተሠኘ የሙዚቃ አልበም ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም ለህዝብ እንደሚደርስ ዛሬ በተሰጠ መግለጫ ተነግሯል።

13 ሙዚቃዎችን በውስጡ የያዘው “ውብ ዓለም” አልበም አቤል ሙሉጌታ፣ አቡዲ፣ ኢንጂነር ፋንታ ወጨፎ ፣ ናትናኤል ግርማቸው፣ ጥላሁን ሰማው፣ ፍሬዘር አበበወርቅ ፣ብዘአየሁ አርአያ በዜማና ግጥም ድርሰት የተሳተፉ ሲሆን
በሙዚቃ ቅንብር አዲስ ፈቃዱ፣ ታምሩ አማረ፣ ፋኑ ጊዳቦ ድምፅ ቅጂ ሱራፌል ቻላቸው፣ ሚክስ ማስተር ሠለሞን ኃ/ማርያም፣ ቤዝ ዮሐንስ ብርሃኔ፣ ልዋም መሀሪ፣ ሳክስፎን ዘሪሁን በለጠ፣ ለታሪክ ጥላሁን ጊታር ስብሀት እንዳለ አማኑኤል ወርቁ፣ ማሲንቆ ደግሠዉ አበበ፣ ክራር በረከት ባዩ፣ ተቀባይ አለምዬ ጌታቸዉ፣ አብርሀም በላይነህ፣ ማስተዋል እያዪ፣ ደሜ ሉላ፣ ይድነቃቸው ገለታ፣ ቃል ኪዳን እየሩሳለም በየነ ተሳትፈዉበታል::

ናሆም ሬከርድስ የአልበሙ ኤክስኪዉቲቭ ፕሮዲዉሠር ሲሆን አልበሙ በመጪው ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በናሆም ሬከርድስ የዩቲዩብ ቻናል እና በአለም አቀፍ የሙዚቃ ማሠራጫ እና መገበያያ በሆኑት እንደነ ሲዲቤቢ፣ ዲዘር፣ ስፖቲፋይ እና ሌሎች ታዋቂ መተግበሪያዎች በኩል ለህዝብ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

#ኪነ_ጥበብ





1 comment

Kumbi Ketema July 17, 2025 - 1:01 pm

ኢየሱስን ሳትቀበሉ እንዳት ሞቱ
Life’s Dark With Out Jesus
Iyasuusiin alaa jireenyi dukkana

Reply

Leave a Comment